የአንድነት ፓርቲ ክፍፍል | ኢትዮጵያ | DW | 24.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአንድነት ፓርቲ ክፍፍል

ከሰባት ዞኖች የተወጣጡ የፓርቲዉ አመራር አባላት እንደሚሉት የፓርቲዉ ብሔራዊ ምክር ቤት የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ በላይ በፈቃዱን መተካቱ ሕገ-ወጥ ነዉ

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት)ከአንድነት ይልቅ ወደ-ሁለት ወይም ወደከዚያ በላይነት እያመራ ይመስላል።የቀድሞዉ ፓርቲዉ ፕሬዝዳንት ሥልጣን ለቀዉ በሌላ መተካታቸዉን በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፓርቲዉ ተወካዮች ዛሬ ተቃወመዉታል።ከሰባት ዞኖች የተወጣጡ የፓርቲዉ አመራር አባላት እንደሚሉት የፓርቲዉ ብሔራዊ ምክር ቤት የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ በላይ በፈቃዱን መተካቱ ሕገ-ወጥ ነዉ።ባለሥልጣናቱ ዛሬ በጠሩት ጉባኤ ኢንጀነሩ ሥልጣን እንዲለቁ የተገደዱት ዉጪ ሐገር በሚኖሩ የፓርቲዉ ድጋፊዎች ግፊት።አዲሱ ፕሬዝዳንት የተመረጡትም ጠቅላላ ጉባኤ ሳይጠራ፤ የምርጫ ቦርድ ተወካይም ሳይጋበዝ ነዉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic