የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር | ኢትዮጵያ | DW | 31.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ እሁድ ታኅሣሥ 20 ቀን፥ 2006 ዓም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራውን በከፍተኛ ድምፅ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።

«አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ» እሁድ ዕለት የመረጣቸውን አዲሱ ሊቀመንበሩን በተመለከተ ከፓርቲው አመራሮች አንዱ የሆኑት አቶ ስዩም መንገሻን ደውዬ አነጋግሬ ነበር። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ ከትናንት በስትያ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራውን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቸኛው የምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ግርማ ሠይፉ እና በኋላ ላይ ራሳቸውን ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ውድድሩ ያገለሉት አቶ ተክሌ በቀለ ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸውም ተነግሯል። አቶ ስዩም መንገሻ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ፓርቲው ታኅሣሥ 19 እና 20 በጠራው የልዩ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው። አንድነት ፓርቲ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል። የምርጫ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር? ስል የመጀመሪያ ጥያቄን አቀረብኩላቸው። አንድነት ፓርቲ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመዋሀድ ተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ እንደሆነና ይህን የውህደት ጥሪ የፓርቲው አዲሱ ሊቀመንበርም አበክረው ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic