የአንድነት አመራር አባላት ስሞታ | ኢትዮጵያ | DW | 11.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአንድነት አመራር አባላት ስሞታ

በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙትን አባላቶቻቸውን ለመጠየቅ ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ወደ ማረሚያ ቤቱ ቢሄዱም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ ስለሌሉ መግባት አትችሉም ተብለው ሳይጠይቋቸው መመለሳቸውን የድርጅቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ፣ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል ።

default

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት አዲስ አበባ በሚገኘው ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የታሰሩ የቀድሞ የድርጅቱ አመራር አባላትን እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን አስታወቁ ። በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙትን አባላቶቻቸውን ለመጠየቅ ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ወደ ማረሚያ ቤቱ ቢሄዱም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ ስለሌሉ መግባት አትችሉም ተብለው ሳይጠይቋቸው መመለሳቸውን የድርጅቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ፣ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል ። ሃላፊው ክልከላው በህግ ጥበቃ ሥር ስለ ሚገኙ ዜጎች በህገ መንግሥቱ የተደነገገውን አንቀፅ የሚጥስ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic