የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰነዘረዉ ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 11.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰነዘረዉ ክስ

የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መንግሥት በፓርቲዉ አመራርና አባላት ላይ የሚሰነዝረዉን ማዋከብ ከምንጊዜዉም በላይ አጠናክሮ ቀጥሎአል ሲል ከሰሰ።


ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የፓርቲዉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን እንደገለፁት በሀገሪቱ ሊደረግ የታቀደዉን ብሔራዊ ምርጫ አስመልክቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚሰነዘረዉ ወከባ መንግስት የፖለቲካ እንቅስቃሴዉን ለመቆጣጠር ሆነ ብሎ እያደረገ ያለዉ ተግባር ነዉ።
እንደ ሁልጊዜዉ ሁሉ አሁንም የፓርቲዉ አባላት ላይ እስራት፤ እንግልትና ወከባ ይፈፀምባቸዋል፤ ያሉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ለሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮች እስርና ወከባ መፍትሄ አይሆንም የሚል መግለጫ ፓርቲያቸዉ ማዉጣቱን ገልፀዋል። ይህ ደግሞ በመጪዉ ግንቦት በሚደረገዉ ብሄራዊ ምርጫ ላይ ፓርቲዉ እንዳይሳተፍ የተወሰደ ርምጃ ነዉ ያሉት አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን። ሙሉ ቃለ-ምልልሱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic