የአቶ አንዳርጋቸዉ እገታና የመብት ተሟጋቹ ተቋም | ኢትዮጵያ | DW | 07.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአቶ አንዳርጋቸዉ እገታና የመብት ተሟጋቹ ተቋም

የአዉሮጳ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመን-ርዕሠ ከተማ ሰነዓ አዉሮፕላን ማረፊያ ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ ተግዘዋል የተባሉትን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ለማስፈታት እንዲጥሩ «ጊዜልሻፍት ፉር ብድሮተ ፎልከር» የተሰኘዉ የጀርመን የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ።

Schnell Wachsende Städte Sanaa

ሰነዓ ከተማ

ለተጨቆኑ ሰዎች ጥብቅና የቆመዉ ድርጅት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ አቶ እንዳርጋቸዉ ፅጌንም ሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የታሠሩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ለማስፈታት የአዉሮጳ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ጣልቃ መግባት አለባቸዉ።

Flash-Galerie Airbus A 350 800 XWB

የመን አየር መንገድ


GESELLSCHAFT FÜR BEDROHTE VÖLKER «ጊዜልሻፍት ፉር ብድሮተ ፎልከር» በማለት የሚታወቀዉ በጀርመን ጎቲንገን ከተማ የሚገኘዉ ለተጨቆኑ ሰዎች ጥብቅና የቆመዉ ድርጅት የአዉሮጳዉኅብረት እና የተመ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒላይ፤ የት እንደደረሱ እስካሁን በግልፅ ያልታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ መሪ የአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ የት እንደሚገኙና፤ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንዲያደርጉ ጠየቀ።«ለዲሞክራሲያዊትዋ ኢትዮጵያ የሚናገሩት የታዋቂዉ የተቃዋሚዎች መሪ የአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ደህንነት እጅግ አሳስቦናል ሲሉ የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ኃላፊ ኡልሪሽ ዲሉስ ዛሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል። በእዉነት በአሁኑ ወቅት አቶ እንዳርጋቸዉ ፅጌ የት እንደሚገኙ ድርጅታቸዉ የሚያዉቀዉ ነገር የለምን?
«በጣም ከባድ ነዉ በአሁኑ ግዜ ያለዉን መረጃ ሁሉ መመርመር ያስፈልጋል። በሳምንቱ መጠናቀቅያ ላይ የተቃዋሚዎች መሪ እንዳርጋቸዉ ፅጌ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈዉ ተሰጥተዋል የሚል ዘገባ በተደጋጋሚ ተነቧል፤ ተሰምቶአል። እስካሁን ግን ይፋዊ ማረጋገጫን አላገኘንም። በዚህም የአዉሮጳዉ ኅብረት እና የተመ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር መጀመርያ የአንዳርጋቸዉ ፅጌን የደህንነት ሁኔታ እንዲያጣሩ ፤ ማለትም በየመን የፀጥታ ጥበቃ ሥር መሆናቸዉን እልያም ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈዉ

Gesellschaft für bedrohte Völker Logo Grafik

የጀርመኑ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አርማ

መሰጠታቸዉን አጣርተዉ ፤ የተረጋገጠ መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀናል። በርካቶች እንደሚገልፁት፤ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈዉ መሰጠታቸዉን እያወሩ ነዉ፤ እኛ ግን እስካሁን ምንም አይነት ማረጋገጫ አላገኘንም። ስለዚህም የት ቦታ እንደሚገኙ እንዲጣራ ጠይቀናል»
ኢትዮጵያ በአሸባሪነት ለዓመታት ስትፈልጋቸዉ የነበረዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የግንቦት ሰባት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ፤ ከሰኔ 16 አዉሮፕላን ለመቀየር ሰንዓ አየር ጣብያ ሳሉ በፀጥታ አስከባሪዎች ከተወሰዱ በኃላ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ግዜ ድረስ ያሉበት በግልፅ አልታወቀም። በሳምንቱ መጨረሻ ፓርቲያቸዉ ባወጣዉ መግለጫ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈዉ ተሰተዋል። ይን በማያያዝ አቶ አንዳርጋቸዉ በኢትዮጵያ የሚጠብቃቸዉ እድሜ ይፍታህ እስር አልያም የሞት ቅጣት መሆኑን ለተጨቆኑ ሰዎች ጥብቅና የቆመዉ ድርጅት ስጋቱን ባወጣዉ መግለጫ አስነብቦአል፤
«ነገሩ አሳፋሪ እና ትርጉም የለሽ ነዉ። ግለሰቡ በዜግነት እንግሊዛዊ ናቸዉ ። አዉሮፕላን ለመቀየር ማለት ትራንዚት ለማድረግ ባረፉበት ሀገር በቁጥጥር ሥር ማዋልና እያደናቸዉ ወዳለዉ ሀገር መንግሥት አስተላልፎ መስጠት ተቀባይነት የሌለዉ ሥራ ነዉ። እኝህ ፖለቲከኛ በኢትዮጵያ በአሸባሪነት ወንጀል ፤ በባልሠሩት የተወነጀሉ፤ እና ለዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ሲፈልጋቸዉ እንደነበር በግልፅ ይታወቃል። በኢትዮጵያም ትክክለኛ ፍርድ እንደማይጠብቃቸዉ በግልፅ እናዉቃለን። እዚህ ላይ ጉዳዩ አሸባሪነት ሳይሆን በመንግስት ላይ ትችትና ሂስ የሚያቀርቡ በዓለም ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ፖለቲከኛ አፍ ለማዘጋት የተደረገ ርምጃ ነዉ። ሥለዚህም ጥያቄያችን የአዉሮጳዉ ኅብረት ይህ ፖለቲከኛ በዚህ ፍርድ ላይ እንዳይቆሙና በነፃ ወደ ብሪታንያ እንዲለቀቁ አስቸኳይ ጫና እንዲያደርግ ነዉ። ይህ ካልሆነ ደግሞ በአዉሮጳ በብሪታንያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለዉ ግንኙነት ሥጋት ላይ ይወድቃል።»

Karte Äthiopien englisch


የድርጅቱ መግለጫ ከአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እንዲሁም ባለፈዉ የሳምንት መጨረሻ ዳግም በርካቶች ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡበት የታሠሩ የሙስሊም መሪዎች እንዲፈቱ ይጠይቃል፤ ዲሊዩስ በዚህ ጉዳይ የላሉ
«ሁኔታዉ በጣም ከባድ ነዉ። ኢትዮጵያ ዲሞክራስያዊ መርህን ይዛ እንድትራመድ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት የሚታየዉ ችግርን፤ ለመቅረፍ ምንም አይነት የፈዉስ መድሃኒት አላገኘንም። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይደረጋል። በተለያዩ ጎሳዎች፤ የኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ባጠቃላይ በጋዜጠኞች እና በፕሪስ ነፃነት ላይ የሚደረግ ከፍተኛ ጫና እና የመብት ጥሰት አለ። በዚህም የአዉሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ትክክለኛ መንግሥትና የሀገር መሪ እንዲመጣ፤ በተጨማሪም ለዲሞክራሲ ሰፊ የሥራ ቦታ እንዲፈጠር እንዲያደርግ ጥያቄ እያቀረብን ነዉ። በኢትዮጵያ ይህ ሁሉ የለም። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዉስጥ በፊደራል መንግሥት ስር ያለዉ መንግሥት የአንድ ቡድን ክምችት፤ የራሱን ፍላጎት ብቻ ሌሎች እንዲሰሩ የሚስገድድ ጨቋኝ መንግሥት ነዉ፤ የአዉሮጳ ኅብረት በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲሰራ ጠይቀናል»

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic