የአቶ አሰፋ ጫቦ ኅልፈት | ኢትዮጵያ | DW | 25.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአቶ አሰፋ ጫቦ ኅልፈት

በንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት ለጥያቄ እና መልስ ውድድር  ወደ አሜሪካን ሀገር ተልከው ያሸነፉ እና ከንጉሡም የወርቅ የእጅ ሰአት የተሸለሙት ዕውቁ ፖለቲከኛ አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57

የአቶ አሰፋ ጫቦ ዜና ዕረፍት

በንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት ለጥያቄ እና መልስ ውድድር  ወደ አሜሪካን ሀገር ተልከው ያሸነፉ እና ከንጉሡም የወርቅ የእጅ ሰአት የተሸለሙት ዕውቁ ፖለቲከኛ አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ። ጸሐፊ፣ የሕግ ባለሞያ እና የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ አሰፋ ጫቦ በደርግ ዘመነ-መንግሥት ለ10 ዓመት ከመንፈቅ ታስረው እንደተፈቱ  በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። በኢሕአዴግ አገዛዝ ደግሞ ከሀገር ተሰደው ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ አድርገው ነበር።  ከረዥም ዓመታት የጽሞና ጊዜ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ ብቅ ብለው በተከታታይ ጽሑፎችን ያቀርቡ ነበር። ባለፈው እሁድ በተወለዱ በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጧል። ስለ አቶ አሰፋ ጫቦ የሕይወት ታሪክ  ዶክተር ካሳ ከበደን በማናገር መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።  

መክብብ ሸዋ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic