የአቶ አሥራት ጣሴ ይግባኝ | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአቶ አሥራት ጣሴ ይግባኝ

አቶ አስራት ዛሬ በጠበቃቸው በኩል ለልዩ ችሎቱ ባቀረቡት ይግባኝ በአንድ የግል መፅሄት ላይ ፍርድ ቤቱን በመድፈርና በመተቸት ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የተጣለባቸው የ2 ዓመት ገደብ እንዲነሳላቸው ጠይቀው ነበር ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተና ፍርድ ቤት 11ኛ ይግባኝ ሰሚ ልዩ ችሎት ለአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል ለአቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ ። አቶ አስራት ዛሬ በጠበቃቸው በኩል ለልዩ ችሎቱ ባቀረቡት ይግባኝ በአንድ የግል መፅሄት ላይ ፍርድ ቤቱን በመድፈርና በመተቸት ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የተጣለባቸው የ2 ዓመት ገደብ እንዲነሳላቸው ጠይቀው ነበር ። ሆኖም ችሎቱ ይግባኙ ረዝሟል ሲል ፍሬ ነገሩ ላይ አትኩሮ አጠር ብሎ እንዲቀርብለት በማዘዝ ለሚያዚያ አንድ ቀን 2006 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic