የአቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ | ኢትዮጵያ | DW | 13.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ

የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት የሚባሉት እና ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓም በ90 አመታተው ያረፉት የአቶ ሐብተ ሥላሴ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ ተፈጸመ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:18
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:18 ደቂቃ

አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ

ብዙ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ ትልቅ አስተዋፅዎ ያበረከቱት አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ ዕሮብ ዕለት በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ ሐብተ ሥላሴ የኢትዮጵያን «የ13 ወር ፀጋ» የሚለውን የቱሪዝም ማስተዋወቅያ የፈጠሩ እና ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት የለፉ ናቸው። ለሚደነቀው አስተዋጾዋቸውም የኢትዮጲያ ቱሪዝም አባት እየተባሉ ይጠራሉ።

የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በቀብር ስነ-ስርዓታቸው ላይ ተገንቶ አቶ ሐብተ ሥላሴ እንዴት እንደሚታወሱ ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic