የአቶም ሳይንቲስቱ ዶ/ር ጌድዮን ጌታሁን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአቶም ሳይንቲስቱ ዶ/ር ጌድዮን ጌታሁን

ዶክተር ጌድዮን የሚሰሩት ጀርመን ቢሆንም ሃገራቸውንና ህዝባቸውን አልረሱም ለረዥም ጊዜ በሊቀመንበርነት በሊቀመንበርነት በመሩት ማህበር አማካይነትና በግላቸው የኢትዮጵያን የሳይንስ ትምሕርትና ተማሪዎች ይረዳሉ ።


ቀጣዩ አውሮፓና እዚህ ጀርመን ከተማሩና ለበርካታ አመታት ከሰሩ አንድ የአቶም ሳይንቲስት ጋር ያስተዋውቀናል ።

በምዕራብ ጀርመኑ የራይንላንድፋልስ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ማይንዝ በሚገኘው ዪሐንስ ጉተንበርግ ዩኒቨርስቲ የአቶም ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ናቸው ። ካለፈው አመት ጀምሮ ደግሞ ዳርምሽታት በተባለው ከተማ ውስጥ በሚካሄድ የምርምር ሥራ ተካፋይ ናቸው የዛሬው እንግዳችን ዶክተር ጌድዮን ጌታሁን ።
የራድዮ አናሊቲካል ኬሚስትሬ ምሁር ዶክተር ጌድዮን የሙያቸውን ምንነትና ጥቅሙን በቅድሚያ ይነግሩናል ።

Johannes Gutenberg-Universität Mainz, Hauptportal, eingestellt am 22.12.2009, Foto: Hartmann Fotodesignዶክተር ጌድዮን ጀርመን ለትምህርት የመጡት በ1966 ሲሆን መጀመሪያ በባየርንዋ ሙርናው ከተማ የቋንቋ ትምሕርት ከተከታተሉ በኋላ በሽቱትጋርት የኬምስትሪ ትምሕርት ከተከታተሉ በኋላ እዚያው ሽቱትጋርት ውስጥ ሥራ ያዙ ። ከዚያም ወደ ዳርምሽታት በመሄድ የኬሚካል ኢንጅነሪንግ ትምሕርት ተከታትለው በኋላ በዚያ ከተማ ለረዥም ጊዜ በፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ሰሩ ። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ሌላ ትምህርት የመከታተል እድል አገኙ ። ዶክተር ጌታሁን የአቶም ሳይንስ ለማጥናት ሲወስኑ ምክንያት ነበራቸው ።
ከ1995 አም አንስቶ በማይንዝ የኒዩክልየር ሳይንስ ተቋም ሥራ አግኝተው አሁን እዚያው በመሥራት ላያይ ናቸው ። ዶክተር ጌታሁን ከዚህ ሌላ ለከተማዋ የ SPD ፓርቲ በሞያቸው እያገለገሉ ነው

In this photo taken Sunday, March 20, 2011, wind turbines are seen at sunset in Nauen, Germany. Germany stands alone among the world's leading industrialized nations in its determination to abandon nuclear energy for good because of the technology's inherent risk. Europe's biggest economy is betting billions on expanding the use of renewable energies to meet its demand instead. The transition was supposed to happen slowly over the next 25 years, but now it is being accelerated in the wake of Japan's Fukushima disaster. Chancellor Angela Merkel said the catastrophe of apocalyptic dimensions irreversibly marks the start of a new era. (AP Photo/Ferdinand Ostrop)


ምንም እንኳን ዶክተር ጌድዮን የሚሰሩት ጀርመን ቢሆንም ሃገራቸውንና ህዝባቸውን አልረሱም ለረዥም ጊዜ በሊቀመንበርነት በሊቀመንበርነት በመሩት ማህበር አማካይነትና በግላቸው የኢትዮጵያን የሳይንስ ትምሕርትና ተማሪዎች ይረዳሉ ።
ዶክተር ጌታሁን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት የኬምስትሪ ትምሕርትን ለማስፋፋፋት ወከናወን ያለባቸውን ተግባራት ጠቁመዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic