የአትሌት ታምሩ ደምሴ ተቃውሞ | ስፖርት | DW | 13.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የአትሌት ታምሩ ደምሴ ተቃውሞ

በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው 15ኛው የፓራ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ባለፈው እሁድ በ1500 ሜትር ሩጫ ውድድር የብር ሜዳሊያ ለሀገሩ ያስገኘው ታምሩ ደምሴ የተቃውሞ ምልክት ማሳየቱ አሁንም እያነጋገረ ይገኛል፡፡

የተቃውሞ ምልክቱን በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይም የደገመው ታምሩ ድርጊቱን ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ ለዓለም ህዝብ ለማሳየት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ታምሩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይፈልግ እና ከዓለምአቀፉ ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴ እገዳ ሊጣልበት እንደሆነ መስማቱን ለዶየቸ ቨለ ገልጿል፡፡ በእንግድነት ብቅ ያለው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከሌሊሳ ፈይሳ በኋላ በኦሎምፒክ መንደር በድጋሚ ተቃውሞውን ያሳየውን አትሌት ታምሩን አነጋግሮታል፡፡አትሌቱ በውድድሮች ላይ ስለነበረው ተሳትፎ በመግለጽ ይጀምራል።

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic