የአብርሀም ሊንከልን ሁለት መቶኛ የልደት በዓል መታሰቢያ | ዓለም | DW | 12.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአብርሀም ሊንከልን ሁለት መቶኛ የልደት በዓል መታሰቢያ

በዩኤስ አሜሪካ ከፍተኛ ዝና ያተረፉት የአስራ ስድስተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አብርሀም ሊንከልን ሁለት መቶኛ የልደት በዓል

አብርሀም ሊንከልን

አብርሀም ሊንከልን

ዛሬ በመላይቱ ሀገር በደመቀ ስነ ስርዓት በመታሰብ ላይ ይገኛል። አብርሀም ሊንከልን ሀገሪቱን በማዋሀድና የባርያ አሳዳሪ ስርዓትን በማስወገዳቸው ይታወቃሉ። አብርሀም ሊንከልን የሚያደንቁትና የኒሁን ታዋቂ ፕሬዚደንት የአመራር ስልትን እንደቀሰሙ የሚናገሩት አዲሱ የዩኤስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በኢሊኖይ ስፕሪንግፊልድ በተዘጋጀው የሊንከልን መታሰቢያ ራት ግብዣ ላይ ይገኛሉ። የሊንከልንን መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ዛሬ በስማቸው አራት ቴምብሮች እና ፕሬዚደንታዊ ሳንቲሞች ወጥተዋል። አበበ ፈለቀ

AA, SL