የአባይ ግድብ አጥኚ ድርጅት እራሱን አገለለ | ዓለም | DW | 15.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአባይ ግድብ አጥኚ ድርጅት እራሱን አገለለ

የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:59
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
01:59 ደቂቃ

የአባይ ግድብ አጥኚ ድርጅት እራሱን አገለለ

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ የኤሌክትሪክ ሐይል ማመንጫ ግዙፍ ግድብ በወንዙ ፍሰት ላይ የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ ከመረጧቸዉ አጥኚ ተቋማት አንዱ እራሱን ከጥናቱ አገለለ።ዴልታሬስ የተሰኘዉ የኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ተቋም እራሱን ከጥናቱ ያገለለዉ ከሌላዉ አጥኚ ተቋም (BRL በምሕፃሩ ከተሰኘዉ ከፈረንሳዩ ተቋም) ጋር ባለመግባባቱ ነዉ።የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የዴልታሬስን ቃል አቀባይን አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሠ

Audios and videos on the topic