1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም

ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016

ጀርመናዉያን ስለ ስዕል ያላቸዉ አመለካከት በጣም ድንቅ ነዉ። የስዕል እግዚቢሽን በዘረጋሁ ቁጥር አስተያየት የምቀበልበት ሦስት ትልልቅ ደብተሮቼ በአስተያየቶቻቸዉ ሞልቷል። ከአስተያየቶቹ መካከል “አንቺ ወደዚች ዓለም የመጣሽባትን የቤት ሥራ አግኝተሽዋል” ሲሉ ጽፈዉልኛል። ሌሎች ደግሞ “የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ” ብለዉ ነዉ የሳልኩትን አበባ የሰየሙት።

https://p.dw.com/p/4hZTS
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ምስል Abaynesh Mannheim

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም

 
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊት አባይነሽ ማንሃይም 


«ጀርመናዉያን ስለ ስዕል ያላቸዉ አመለካከት በጣም የተለየ እና ድንቅ ስለሆነ፤ የስዕል እግዚቢሽን በዘረጋሁ ቁጥር አስተያየት የምቀበልበት ሦስት ትልልቅ ደብተሮቼ በአስተያየቶቻቸዉ ሞልቷል። ከአስተያየቶቹ መካከል “አንቺ ወደዚች ዓለም የመጣሽባትን የቤት ሥራ አግኝተሽዋል” ሲሉ ጽፈዉልኛል። በእድሜ ጠና ያሉት ጀርመናዉያን ደግሞ “የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ” ብለዉ ነዉ በስዕል ያስቀመጥኩትን አበባ የሰየሙት። ስለኢትዮጵያ የሚያዉቁትን፤ በተለይ ስለ አፄ ኃይለሥላሴ ሁሉ አንስተዉ ነገሮችን አገናኝተዉ ስለኢትዮጵያ ይነግሩኛል»    
ቀለም እና የምስልበትን ሸራ እንደ ቦርሳዬ በሄድኩበት ይዤ እና አንጠልጥዬ ነዉ ነዉ የምሄደዉ ስዕል ህይወቴ ነዉ፤ የእየለት መግቤ ነዉ፤ ሲሉ የነገሩን ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ይባላሉ። የአቢሲኒያ ጽጌሬዳ ሲሉ ጀርመናዉያን አድናቂዎቻቸዉ የሚጠርዋቸዉ ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም፤ አብዛኞች ስዕሎቻቸዉ ጽጌሬዳ አበባ በመሆኑ እንደሆን ነግረዉናል። በደቡብ ጎንደር ተወልጄ ንፋስ መዉጫ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ተምሪያለሁ። ንፋስ መዉጫ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ፤ በእርዳታ ድርጅት ተቀጥሪ ለሦስት ዓመታት አገለግልም ነበር ፤ ስዕል የጀመርኩት ወልድያ ስኖር ነዉ ሲሉም አጫዉተዉናል። በጀርመን ሲኖሩ 26 ዓመት የሆናቸዉ ሰዓሊአባይነሽ ከንፋስመዉጫ ወደ አባታቸዉ ሃገር ወደ ወልድያ ሄደዉ ሲኖሩ ሳለ ነበር ጀርመናዊዉን ባለቤታቸዉን የተዋወቁት። 

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ምስል Abaynesh Mannheim

ደቡብ ጎንደር ነፋስመዉጫ
«የተወለድኩት በቀድሞ ጊዜ ጎንደር ክፍልሃገር በሚባለዉ፤ በደቡብ ጎንደር፤ ሮቢት በምትባል ሙጃ በምትባል ትንሽ ከተማ ዉስጥ ነዉ። ትምህርቴን እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የተማርኩት በንፋስ መዉጫ ከተማ ነዉ። ከዝያም ለሦስት ዓመታት በዝያዉ በንፋስ መዉጫ በአንድ እርዳታ ድርጅት ዉስጥ አገልግያለሁ። ወያኔ የኢትዮጵያን ስልጣን ሲቆጣጠር ከንፋስ መዉጫ ወደ አባቴ አገር ወደ ወልድያ ሄድኩ። የምኖረዉ በወልድያ ከተማ አክስቴ ጋር ነበር። በዝያ ትንሽ እንደቆየሁ ሴንትራል የሚባል ሆቴል ቤት ከፍቼ ጥሩ እየሰራሁ ለስድት ዓመታት ዘልቄያለሁ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ለመንግድ ስራ ወደ ወልድያ የመጣ አንድ የጀርመን ተቋም ዉስጥ የሚሰራ ባለቤቴን ተዋኩት። ጀርመናዉያኑ ምግብ የሚበሉት እኔ ሆቴል ቤት እየመጡ ነበር። ቆይቼ ወደ ጀርመን ከባለቤቴ ጋር መጣሁ። አሁን ጀርመን ሃገር መኖር ከጀመርኩ 26 ዓመት ሆኖኛል።»    
በጀርመን ባቫርያ ግዛት ሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም፤ ስዕልን ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ከተፈጥሮ ያገኙት ሞያ መሆኑንም ነግረዉናል። ይሁን እና የስዕል አያያዙን አጣጣሉን፤ የተገሩት በወላጅ እናታቸዉ መሆኑን አልደበቁንም። 
«እናቴም አባቴም ባለሞያዎች ናቸዉ። በእርግጥ እናቴ የስዕል ተሰጦ አላት ያደኩትም ከእናቴ ጋር ነዉ። ከልጅነቴ ጀምሬ እቤት ዉስጥም ትምህርት ቤትም እጄ ስራ ፈቶ አያዉቅም ነበር፤ እስላለሁ፤ የእጅ ስራ እሰራለሁ። ጥሩ የአልጋ ልብስ እሰራ ነበር። የእጅስራዉ የስዕል ስራዉ በተፈጥሮ ያገኘሁት ነዉ። ጀርመን ሃገር ከመጣዉ በኋላ የተለያዩ የስዕል አጫጭር ትምህርትን ተምሬ የቀል አጣጣልን ተምሬያለሁ። ከዝያ በኋላ ጀርመን ሃገር 26 ዓመት ስቀመጥ ወደ 30 ጊዜ የስዕል እግዞቢሽን ዘርግቻለሁ። በዚህ ጊዜ ያገኘኋቸዉ ጀርመናዉያን የአቢሲኒawa ጽጌሬዳ ሲሉ ስዕሌን ያደንቃሉ፤ ኢትዮጵያዉያን ሰዓሊያን ናቸዉ እያሉ ስለ አፄ ኃይለሥላሴ እያነሱ ያደንቃሉ፤ ይነግሩኝማል።» 

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ምስል Abaynesh Mannheim

እናቴ የስዕል አሳሳልን ያስተማሩኝ የመጀመርያዋ ናቸዉ
ሰዓሊ አባይነሽ ስዕልን በልጅነትዎ እንደጀመሩት ብሎም ከወላጅ እናቶ እንደተማሩ ነግረዉኛል። እና በዝያን ጊዜ ቀለምን እና ሸራን ቡሩሽን ከየት ነበር የሚያገኙት እንዴት ነበር የምትስሉት? 
«አገሬ ሳለሁ፤ በከሰል ኖራን እየወሰድኩ ነበር ግድግዳ ላይ እበት በtl,ቀለቀ ነገር ላይ n።በር የምስለዉ ። ቀይ አፈር ወይም ሸክላም እንዲሁም አደይ አበባን እጠቀም ነበር። እናቴ ነበር የምታሳየኝ።  ስዕሎቼ  ፤ ጎጆቤት፤ የዛፍ፤ ጫካ አበባ፤ ወይም ሰዉ ነበር ግድግዳ ፤ላይ የምስለዉ።  ቆይቼ በእርሳስ ቆንጆ አበባን ወረቀት ላይ እስል ነበር። በክር ደግሞ በኪሮሽ አበባ ያለበት ቆንጆ የአልጋ ልብስ እሰራ ነበር። በዝያዉ ነዉየስዕል ስራን እየገፋሁበት የመጣሁት። ልጄ እንዲስል እኔም እናቴ እንዳደረገችዉ ልጄን ስዕል እንዲስል ሞክሬ ነበር ግን በስዕሉ አልገፋበትም።» 
እና ኢትዮጵያ ዉስጥ ሳሉ ይህን የስዕል ችሎታዎችን ለማዳበር ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም?  
«እንደሚታወቀዉ በኢትዮጵያ በዝያ ወቅት የስዕል ትምህርት ቤት አልነበረም። በተለይ እኔ በምኖርበት በወልድያ የስዕል ትምህርት ቤት አልነበረም ነገር ግን በትምህርት ቤት በእጅ ስራ ክፍለ ጊዜ እኔ ሁልጊዜ የምገኘዉ ስዕሉ ላይ ነበር። በወልድያ ስኖር ደግሞ ሙሉ ጊዜዬን የሰጠሁት በንግዱ ስራ ላይ ነበር። በሌላ በኩል የአራት ልጆች እናት በመሆኔም ብዙ ለስዕል ጊዜ አልነበረኝም። ከወልድያ ወደ ጀርመን ከመጣሁ ወዲህ ግን ስዕሌን ዳግም መሳል ጀመርኩ።» 

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ምስል Abaynesh Mannheim

 


ወደ ጀርመን ከመጡ በኋላ ስዕሎን እንዴት ቀጠሉ? ይህንን ሞያዎን ለመቀጠለስ አልተደናገሮትም? 
« አልተደናገረኝም፤ ወደ ጀርመን ከመጣሁ በኋላ የሥዕል ትምህርት ቤት የነበራቸዉ አንድ ጀርመናዊ ፕሮፌሰርን ተዋዉቄ ወደ ስዕሉ ዳግም እንድገባ ረዱኝ፤ የስዕል አጫጭር ትህርቶችንም ተማርኩ። በግልም እንዲህ የሚረዳኝ ሰዉ አገኘሁ። ከዝያ ቀለም እና የስዕል መሳያ ሸራ የሚያመጣልኝ ሰዉ በዛ ከዝያም ፤ ተርቤ የነበረዉን የስዕል ፍላጎቴን እንደገና መኖር ጀመርኩ። ጀርመኖችም ለስዕል ለኪነጥበብ ጉዳይ በጣም ጎበዞች ናቸዉ ። ገና ስዕል መሳል እፈልጋለሁ ስላቸዉ ነዉ ፤ ቶሎ ብለዉ ፍላጎቴን ያሟሉልኝ። ከዝያ ጊዜ ወዲህ ስዕሎች እስላለሁ ኤግዚቢሽን አደርጋለሁ። ስዕሎቼን መሸጥ አልወድም ምክንያቱም፤ ወደፊት እንዲህ ልስል አልችልም ለታሪክ ይቀመጥ እያልኩ ነዉ የማስቀምጠዉ።»

«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም
«የአቢሲኒያዋ ጽጌሬዳ» ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ምስል Abaynesh Mannheim

 

በጀርመን አቡዳቢ እና አዲስ አበባ እግዚቢሽን አሳይቻለሁ  
ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ወደ ጀርመን ከመጡ ወደ 30 ጊዜ የሚሆን የስዕል እግዚቢሽን ዘርግተዉ እንደነበር ነግረዉናል። በተለያዩ ጋዜጦችም ስለ ስዕላቸዉ ብሎም ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ተጽፏል። በጋዜጦች ላይ የአቢሲኒዋ ጽጌሪዳ የሚል ርዕስን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት ስለሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም በጀርመን ጋዜጦች ታትሟል።  ሰዓሊ አባይነሽ ከጀርመን ሌላ በዱባይ እና በአዲስ አበባ የስዕል እግዚቢሽን ዘርግተዉ ለተመልካች እንዳሳዩ ተናግረዋል።  
ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም አብዛናዉን ጊዜ አበባን የሚስሉት የፍቅር መግለጫ የተስፋ ማሳያ መሆኑን በማመናቸዉ እንደሁ ነግረዉናል። ሰዓሊዋ አብዛኛዉን ጊዜ የሚስሉት ምሽት ላይ አልያም ለሊት እንቅልፍ እንቢ ሲላቸዉ ለሊትም እንደሚስሉ ነግረዉናል።  በጀርመን በይፋ ጡረታ ላይ የሚገኙት ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ስዕላቸዉ ጓደኛቸዉ፤ መዝናኛቸዉ እሳቸዉ እንደሚሉት ደግሞ እንጀራ ዉኃቸዉ፤ በጀርመን ከሚኖር ማኅበረሰብ ጋር የሚያናኛቸዉ መሳርያ ድልድያቸዉ እንደሆን አጫዉተዉናል። ሰዓሊ አባይነሽ ማንሃይም ለሰጡን ቃለ ምልልስ በ ዶቼ ቬለ «DW» ስም በማመስገን ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ