የአሸባብ ጥቃት በጋሪሳ ኬንያ | አፍሪቃ | DW | 02.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአሸባብ ጥቃት በጋሪሳ ኬንያ

በምሥራቃዊ ኬንያ በጋሪሳ ከተማ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት የጦር መሳሪያ ባነገቱ ሰዎች ጥቃት እንደደረሰበት ተነገረ። በጥቃቱ ቢያንስ 70 ሰዎች መገደላቸውን፣ ወደ 80 የሚጠጉ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሀኪም ቤቶች መወሰዳቸውን ያካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

የቀይ መስቀል አባላት እንዳገለጹት፣ አጥቂዎቹ ብዙ ክርስትያን ተማሪዎችን ያገቱ ሲሆን፣ አንድ የተማሪዎች መኖሪያ ህንጻንም ተቆጣጥረዋል። 50 ተማሪዎች ደግሞ ሸሽተዋል። ከጥቃቱ በኋላ ወደዩኒቨርሲቲው በሄዱት በፀጥታ ኃይላቱ እና በታጣቂዎች መካከል ረዘም ላለ ጊዜ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን የኬንያ ሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ገልጾዋል። የሶማልያ የአሸባብ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል። የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በጥቃቱ ለሞቱት ቤተሰቦች ሀዘናቸውን ፣ ለቆሰሉት ደግሞ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

« በራሴ እና በመንግሥቴ ስም በጥቃቱ ለሞቱት ቤተሰቦች ጥልቅ ሀዘኔን እገልጻለሁ። የቆሰሉትም ቶሎ እንዲድኑ፣ በታጣቂዎቹ እጅ የሚገኙትን ደግሞ የማስለቀቁ ተግባር በደህና እንዲከናወን መጸለያችንን እንቀጥላለን። መንግሥቴ ትክክለኛውን ርምጃ በመውሰድ ጥቃቱ ወደተጣለበት አካባቢ ጦር በማሰማራት ሁኔታውን መቆጣጠሩን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ። »

ኬንያ ከዛሬው የዩኒቨርሲቲ ጥቃት ጋ ግንኙነት አለው የሚባለውን መሀመድ መሀማዱ የተባለውን ሰው ለማሰር የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ ሰው 20 ሚልዮን ሺሊንግ ወሮታ እንደምተሰጥ አስታውቃለች።

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ