የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እና አንድምታዎቹ | ኢትዮጵያ | DW | 19.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እና አንድምታዎቹ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ አርብ ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጇል። አዋጁ የተደነገገውም የሀገሪቱን ሰላም እና መረጋጋት ወደ ነበረበት ቦታ ለመመለስ በሚል መሆኑን የመከላከያ ሚንሥትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ 18 ንዑሣን አንቀጾች ያሉት ሲሆን በዚህ ዉስጥም ብዙ ገደቦችን ማካተቱ ተዘግበዋል። ከነዚህም ዉስጥ ግጭት ሊያስነሱ ይችላል የሚባሉ ፅሁፎችን ማዘጋጀት፣ ማተምና በመገናኛ ብዙሃን ማሰራጨት፤ ምልክቶችን ማሳየት ወይም ማሳወቅ፤ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስ፤ መደራጀት፤ የአደባባይ ሰልፍ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል። በወንጀል የተሳተፈ ወይም የተጠረጠረ ሰዉ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝም በቁጥጥር ሥር እንደሚዉል ይደነግጋል።

የሕግ ባለሙያዉና ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ሚንስትሩ "ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስከበር" ታወጀ  ሲሉ የሰጡትን ምክንያት አይቀበሉም።

መንግስት አገሪቱን ካጋጠማት ችግር ለማዉጣት የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ፤ ሃሳብን በነፃ መግለፅን አከብራለሁ ኢያለ ወደ አስቸኳይ ግዜ አዋጁ መሄዱ ነገሮችን ያከብደዋል የሚሉት ደግሞ የሕግ ባለሙያዉ አቶ ሽብሩ ናቸዉ።

እንድህ ያሉ አስተያየቶችን የሰጡን ቢኖሩም በተቃራኒዉ ደግሞ የአዋጁ ጥቅም ላይ አስተያየቶቻቸዉን ያጋሩንም አሉ። ኢዛና ዘ-አክሱምስ ቭዉ የሚል የፌስቡክ ስም ያለዉ ግለሰብ «የህዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት የታወጀ አዋጅ በመሆኑ አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም» ብሎዋል፡፡ አዋጁ ያስፈለገዉ የአገሪቱ ህልውና ለማስጠበቅ፤ ለውጭ ኃይላት መሳሪያ የሆኑ አመራሮች፣ ግለሰቦችና ቡድኖችንም ለመመንጠር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነውም» ብሎዋል። ሙሉጌታ ገብረፃድቅ በርሄ «ኣዋጁ ተገቢ ቢሆንም በጅምላ መሆኑ እቃወማለሁ» ካለ በኋላ ረብሻ ባለባቸው ክልሎች ለይቶ ማወጅ ሲገባው ሁላችንም በድፍን ታወጀብን» ስልም አስተያየቱን አጋርቶናል።

ሙሉ ዘገባዉን ለማዳመጥ ከላይ ያለዉን ኡዲዎ ይጫኑ።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic