የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታሳሪዎች መለቀቅ | ኢትዮጵያ | DW | 03.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታሳሪዎች መለቀቅ

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተለያዩ እስርቤቶች እንድሁም በፖሊስና ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ታስረዉ ይገኛሉ። ከታሰሩትም ዉስጥ በታህሳስ ወር የመጀመርያ ዙር «የታህድሶ ስልጠና» ወስደዋል የተባሉ ከ11,000 በላይ ሰዎች መለቀቃቸዉ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:00

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታሳሪዎች መለቀቅ

በሁለተኛ ዙር ስልጠና የወሰዱትም ከሳንቃሌ ፖሊስ ማሰልጠና ኮለጅ፣ ከጦላይ ወታደራዊ ካምፕ፣ ከይርጋሌም አፖስቶ ፖሊስ ማሰልጠኛና ከብር ሻለቆ እስር ቤቶች ትላንት መለቀቃቸዉ ተዘግበዋል። መንግስት ሰዎቹን ማሰሩ እንደቅጣት ቢወስድም፣ ታሳርዎቹ ለመተዋወቅና «ትግላቸዉን ለማጠናከር» ጥሩ አጋጣም ሆኖዋል ብለዉ የምካራከሩ አልጠፉም። መርጋ ዮናስ ቀጣይ ዘገባ አለዉ።

ትናንት የተለቀቁት እስረኞችም ባለፈዉ ታሕሳስ እንደተለቀቁት ሁሉ  «የተህድሶ ስልጠና» መዉሰዳቸዉንና በተቃዉሞ ጊዜ በወሰዱት ርምጃ «አይደገምም» የሚል ቃለ መሃለ መግባታቸዉን የመንግሥት መገናኛ ዘዴዎች ዘገባዎች ይጠቅሳሉ።

ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገችዉ ድምፃዊትና የአራት ዓመት ልጅ ህጻን ያላት እናት አራት ወር በጦላይ እስር ቤት  መቆየቷን ትናገራለች። ምን አይነት ስልጠና ነዉ የወሰደችዉ? «አይደገምም» ብላ ቃል የገቡትስ ምንድነዉ? ብዬ ለመጠየቅ ሙከራ ባደርግም ስለሚያማት ብዙም ልታወራ አልቻለችም። ዛሬ ወደ አስር ሰዓት ላይ ከቤተሰቦቿና ከልጇ ጋር ዳግም ትገናኝታለች።

«አሁን ገና ወደ ቤት እየገበዉ ነኝ። አሁን ገና ከመኪና ወርጄ ልጆች እቃዬን ወደ ዉስጥ እየስገቡልኝ ነዉ።ሰዎች ሰላም ሊሉኝ ከጎኔ አሉ። አሁን ለማዉራት ያስቸግራል። እዛ ትንሽ አሞኝ ነበር፣ አንተም ድምፄን እንደምትሰማዉ ትክክል አይደልም። ስለዚህ አሁን ለማዉራትም ትንሽ ያስቸግረኛል።»

ድምጻዊቷ አራት ወር እስር ላይ በቆየችበት ግዜ ህፃኗን ስትንከባከብላት የነበረችዉ ታላቅ እህቷ የንግድ ስራዋን አቋርጣ መሆኑን ለዶቼ ቬሌ ትናገራለች። ድምፃዊቱ ማታ አራት ሰዓት ላይ መታሰረዋን የምትናገረዉ እንዳይገለፅ የፈለገችዉ ታላቅ እህቷ በምን ምክንያት እንደታሰረች ምንም አልተነገረንም ትላለች። የታሳሪዋ ታናሽ እሕት ደግሞ የሚከተለዉን ትላለች።

«መጀመርያ እኔ እናት የለኝም። እሷ ናት እንደ እናት ያሳደገችኝ። ህጄ እስር ቤት ስመለከታትም በጣም በጣም ነዉ ያዘንኩት፣ እናቴ ሁለተኛ እንደሞተች አይነት ስሜት ነዉ የተሰመኝ። የሷዋን ልጅ ትምህርት ቤት እወስዳታለዉ። እናቷንም ብዙ እንዳታስብ ይንከባከባታለዉ።»

መንግስት ታሳሪዎቹን ለመቅጣት ቢያስራቸዉም በሌላ ጎኑ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ታሳርዎች እንድተዋወቁና «ትግላቸዉን» እንድያጠናክሩ እድል ፍጥሮላቸዋል ብሎም የምከራከሩ አልጠፉም። 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ሲጀምር ከታሰሩት ዉስጥ በታህሳስ ወር የመጀመርያ ዙር «የታህድሶ ስልጠና» ወስደዋል የተባሉት ከ11,000 በላይ ሰዎች መለቀቃቸዉ ይታወሳል።ትናንት የተለቀቁትም ከ11 ሺሕ ይበልጣሉ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ 

 

Audios and videos on the topic