የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የመርማሪ ቦርድ ግዴታ  | ኢትዮጵያ | DW | 06.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የመርማሪ ቦርድ ግዴታ 

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ለስድስት ወር የሚዘልቅ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ማወጁ ይታወሳል። ይህም አዋጅ  ስራ ላይ መዋል ከጀመረ ሰሞኑን አምስተኛ ወሩን ያጠናቅቃል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:11

መርማሪ ቦርድ

የአዋጁን አፈፃፀም የሚከታተል ከፓርላማ አባላትና ከሕግ ባለሙያዎች የተወጣጡ ሰባት አባላት ያለዉ የአስቸካይ ግዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ የተሰኘዉ አካል መቋቋሙ ይታወሳል። የአገሮቹ ሕገ መንግስት አንቀፅ 93 ንዕስ አንቀፅ ስድስትም መርማሪ ቦርዱ ያለዉን ስልጣንና ግዴታ ይዘረዝራል። ከዚህም ለቦርዱ ከተሰጡት ስልጣንና ጊዴታዎች መካከል በመንግስት የሚወሰድባቸዉ ርምጃዎች «ኢሰብዓዊ አለመሆናቸዉን መቆጣጠርና መከታተል»፣ እንዲሁም «ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈፅሙትን ሁሉ ለፍርድ እንድቀርቡ ማድረግ» ይሚል ይገኝበታል።

ቦርዱ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩት ግለሰቦች ስማቸዉንና የታሰሩበት ምክንያት በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ይፋ ማድረግ እንዳለበትም በሕገ መንግቱ ይጠቅሳል። ይሁን እንጅ እስካሁን የስም ዝርዝራቸዉና የታሰሩበትን ምክንያት የያዘ የተጠናከረ መረጃ አልታየም። ምን ያህል ሰዉ እንደታሰረ አሁንም አካራካሪ ሆኖ ቢቀጥልም መንግስት በቅርቡ ትምህርት ወሰደዋል የተባሉትን ከ22,000 ባላይ እስረኞች  መልቀቁ ይታወሳል።

የእስረኞቹን የሰብዓዊ መብት አያያዝና የመርማሪ ቦርድን ስልጣን በተመለከተ የሕግ ባለሙያና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ለረጅም ጊዜ ጠበቃ የሆኑት አቶ ታማም አባቡልጉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳሉ ግን ከቦርዱ የተሻለ ዘገባ እንዳማይጠብቁ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

«ኢሰብዓዊ ድርግት የሚፈፅሙትን ሁሉ ለፍርድ እንድቀርቡ ማድረግ» አለበት ሲል ሕገ-መንግስቱ ለቦርዱ የሰጠዉን ጊዴታ ሲወጣ አልታዘብኩትም ሲሉ አቶ ታማም አክለዋል።

ቦርዱ ኃላፊነቱን ምን ያህል ተወጥቷል ብለዉ ያስባሉ ብለንም ከአድማጮቻችን አስተያየት ጠይቀን ነበር። አስተያየታቸዉን በጽሑፍ ከላኩልን ዉስጥ ቦርዱ «በሚገባ ኃላፊነቱን ተወጥቶአል» ያሉ ስኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «ቦርድ የምትሉት በኮማንድ ፓስቱ ቁጥጥር ሰር ከሆነ ቆየ» በማለት አስተያየታቸዉን አጋርተዉናል።

የአዋጅ መታወጁን በተመለከተ ሲጀመርም በቂ ምክንያት አልነበረም የሚሉት አቶ ታማም አባቡልጉ ከአንድ ወር በኋላ አዋጁ ይነል ብለዉ ይጠብቃሉ።

አዋጁ ሰላም አስፍኖአል ከአንድ ወር በኋላም ቢነሳ ከዚህ በኋላ ችግር አይፈጠርም ሲሉ አስተያየታቸዉንም ያጋሩን አሉ። አዋጁ ከስድስት ወር በኋላ እንዲቀጥል ተፈልጎ ለፓርላማ ከቀረበ ቦርዱ «ያለዉን አስተያየት ማቅረብ» እንደሚችል ሕገ መንግስቱም ያሳያል።

መርማሪ ቦርዱ እስካሁን ያጠናቀቀዉ ስራ ካለ የበለጠ መረጃ ለመዉሰድ ሲባል ከመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮችም ይሁን ከመርማሪ ቦርድ አባላቱ ጋር በተደጋጋሚ ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ 
 

Audios and videos on the topic