የአርያና ግራንዲ ዝግጅት እና የለንደኑ ጥቃት   | ዓለም | DW | 05.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአርያና ግራንዲ ዝግጅት እና የለንደኑ ጥቃት  

የ23 ዓመትዋ ወጣት አርያና በማንቼስተር ከተማ ባዘጋጀችው በዚሁ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ሌሎች እውቅ ከያንያንም ተካፍለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:09

የአርያና ግራንዲ ዝግጅት

የብሪታንያ ፖሊስ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ሰባት ሰዎች በተገደሉበት እና 48 ሰዎች ከቆሰሉበት ከለንደን ብሪጁ ጥቃት ጋር  ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ማደን እና ማሰሩን ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የታሰሩት ቁጥር 12 ደርሷል። በብሪታንያ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ለተፈፀመው ለዚሁ ጥቃት ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ሃላፊነቱን ወስዷል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ማደኑን በቀጠለበት በትናንትናው እለት በብሪታንያዋ ሰሜናዊ ከተማ ማንቼስተር ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የአርያና ግራንዲ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጣለው ጥቃት ለሞቱት እና ለተጎዱ ቤተሰቦች መርጃ የተዘጋጀው የሙዚቃ ትርዒት ተካሂዷል። የ23 ዓመትዋ ወጣት አርያና በማንቼስተር ከተማ ባዘጋጀችው በዚሁ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ሌሎች እውቅ ከያንያንም ተካፍለዋል። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳው ጉጌታነህ ዝዝርሩን ልኮልናል ።

ድልነሳው ጉታነህ 

ኂሩት መለሠ

ሸዋዬ ለገሠ

 

Audios and videos on the topic