1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 80 ቀን መታሰቢያ

እሑድ፣ መስከረም 10 2013

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት ዛሬ በአምቦ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን ሲመረቅ በአርቲስቱ ስም የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ  በከተማዋ ተቀምጧል። 

https://p.dw.com/p/3il1Y
Äthiopien 80. Tag Gedenkstätte Haacaaluu Hundessaa
ምስል Seyoum Getu/DW

 

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት ዛሬ በአምቦ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን ሲመረቅ በአርቲስቱ ስም የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ  በከተማዋ ተቀምጧል። በአምቦ ከተማ ደብረብርሃን ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የተሰራው የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የመታሰቢያ ሐውልት የአርቲስቱ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ነው ዛሬ የተመረቀው:: የአርቲስቱ 80 ቀን መታሰቢያ በተደረገበት በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ አርቲስቶችና የአርቲስቱ አድናቂዎች ታድመዋል:: በሌላ በኩል የአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም እንደሚሰየምም ተረጋግጧል።

ስዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ