የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 01.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃዉሞ

ግጭቱ ዛሬ ጋብ ብሎ ነዉ የዋለዉ።ተማሪዎቹ ለግጭቱ መቀስቀስ መንስኤ ያሏቸዉ ወገኖች እንዲጠየቁና የታሰሩ ባልንጀሮቻቸዉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የዩኒቨርስቲዉን ሐላፊዎች በስልክ ለማነጋገር ሞክሮ ነበር

default

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሥጋ ቀለባችን ያለፍቃዳችን ተቀንሶ ለኦሮሚያ ልማት ማሕበር ተሰጠብን በማለት ያነሱት ተቃዉሞ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር አጋጭቷቸዋል።ከተማሪዎቹ መካከል አንዳዶቹ እንደገለፁት በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድበዋል፥ ታስረዋልም።ግጭቱ ዛሬ ጋብ ብሎ ነዉ የዋለዉ።ተማሪዎቹ ለግጭቱ መቀስቀስ መንስኤ ያሏቸዉ ወገኖች እንዲጠየቁና የታሰሩ ባልንጀሮቻቸዉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የዩኒቨርስቲዉን ሐላፊዎች በስልክ ለማነጋገር ሞክሮ ነበር።አልተሳካለትም።የአርባ ምንጭ ፖሊስም ፀጥታ ከማስከበር ሌላ ዝር ዝር መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኘ አልሆነም።

ዩሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic