የአሪዬል ሻሮን የቀብር ሥነ ሥርዓት | ዓለም | DW | 13.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሪዬል ሻሮን የቀብር ሥነ ሥርዓት

እ ጎ አ ከ 2001 – 2006 የእሥራኤል ጠ/ሚንስትር የነበሩትና ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአልጋ ቁራኛ ሆነው የቆዩት አሪዬል ሻሮን ፤ በዛሬው ዕለት በደቡብ እሥራኤል በነጌቭ በረሃ በራሳቸው የአርሻ ቦታ በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ግብዓተ መሬት ተፈጽሞላቸዋል።

የ 17 ዓመት ወጣት ሳሉ ፣ «ሃጋና » የተሰኘው የአይሁድ ነጻ አውጭ የሽምቅ ውጊያ ድርጅት አባል የነበሩት፣ በኋላም ከተራ ወታደርነት እስከ ጀኔራል ማዕረግ የደረሱት አሪዬል ሻሮን፣ እሥራኤል በገጠመቻቸው ከባድ ጦርነቶች ሁሉ የተሳተፉ፤ በተለይ እ ጎ አ በጥቅምት ወር 1973 ከግብፅ ጋር በተካሄደው «ዮም ኪፑር» በተሰኘው ጦርነት በፈጸሙት ጀብዱ፣ ህዝባቸው «የሲናው አንበሳ» የሚል ተቀጥላ ስም በመሥጠት ያሞካሻቸው እንደነበረ ታውቋል ። ስለ ቀድሞው ጠ/ሚንስትር አሪዬል ሻሮን ስንብትና ሥርዓተ ቀብር ከሃይፋ የደረሰን ዘገባ እንሆ---

ግርማው አሻግሬ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic