የአረና ትግራይ አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 20.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአረና ትግራይ አቤቱታ

አረና በድብደባው 10 አባላቱ መጎዳታቸውን ከመካከላቸው 3ቱ አሁንም ድረስ በህክምና ላይ እንደሚገኙም ተናግሯል ። የክልሉ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ስለሁኔታው የደረሰው መረጃ እንደሌለ ለዶቼቬለ አስታውቋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:43

የአረና ትግራይ አቤቱታ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ስር ከተሰባሰቡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው አረና ትግራይ የምርጫ ቅስቀሳ ያካሂዱ የነበሩ አባላቶቹ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው አስታወቀ ። ፓርቲው በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን አፅቢደራ ወረዳ ትናንት ለቅስቀሳ በተሰማሩ አባላቶቹ ላይ በተካሄደ ድብደባ አንዳንዶቹ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል ።አረና በድብደባው 10 አባላቱ መጎዳታቸውን ከመካከላቸው 3ቱ አሁንም ድረስ በህክምና ላይ እንደሚገኙም ተናግሯል ። የክልሉ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ስለሁኔታው የደረሰው መረጃ እንደሌለ ለዶቼቬለ አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሀንስ ገ/እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic