የአረብ አብዮት የገጠመዉ እንቅፋት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2005ማስታወቂያ
የግብፅ ጦር ሐይል በሐገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝዳትን ከሥልጣን ማስወገዱ፥ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ወገኖችን መግደል፥ ማሰሩ ብዙ ሲያነጋግር፥ በሕዝባዊ አመፅ ከስልጣን የተወገዱትና ሰዎች’ በማስገደል የተከሰሱት የቀድሞዉ ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክ ከወሕኒ ቤት ተለቀዋል።ከሁለት ዓመት በፊት የአረቡን ዓለም ያነቃነቀዉ ሕዝባዊ አብዮት ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀጣጠለባት አምባገናናዊዉን ሥርዓት በምርጫ የተኩት የቱኒዚያ ፖለቲከኞች እርስ በርስ እየተወዛገቡባት ነዉ።የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት በቅፅበት ወደ ጦርነት ሲለወጥ፥ የሶሪያዉ የእርስ በርስ ጦርነት ምዕራባዉያንን በቀጥታ ጣልቃ ለማስገባት የመጨረሻ ደረጃ ደርሷል።መፈንቅለ መንግሥቱ፥ ዉዝግብና ጦርነቱ ብዙ ተስፋ የተደረገበት የአረብ ሕዝባዊ አብዮት ፍፃሜ ይሆን? የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ይጠይቃል።መልስ ሰጪም አነጋግሯል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሀመድ
አርያም ተክሌ