የአረብ ሊግ ዉሳኔና የፕረስ ነፃነት | ዓለም | DW | 15.02.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአረብ ሊግ ዉሳኔና የፕረስ ነፃነት

ጋዜጠኛ ኢብሪሽ ዝግጅቱ አይደለም እሱ እራሱ እንዲሕ እየተናገረ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነዉ።የግብፁን ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክን የሚተች ዘገባ በመፃፉ «የሐሰት መረጃ ማሰራጨት


የአረብ ሊግ አባል ሐገራት የማስታወቂያ ሚንስትሮች የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አሠራር በተለመለከተ በቅርቡ ያወጡት ደንብ ተቃዉሞ ገጥሞታል።ሃያ-ሁለት አባል ሐገራትን የሚያስተናብረዉ ማሕበር ደንቡ የአረብን ነባር ባሕል፣ ወግና ማንነትን ለማስከበር ያለመ ነዉ ባይ ነዉ።ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ግን ደንቡ የፕረስ ነፃነትን የሚጋፋ፣ የሕዝብን የማወቅና የመተቸት መብት የሚያፍን ነዉ።ኤሽተር ዛኡብ የፃፈችዉን ዘገባ ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

የግብፁ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ባልደረባ ወኢል ኢብረሺ-ለሚያጠናቅረዉ ዝግጅት «ሐቁ» የሚል ሥም ሰጥቷል።የዛሬ ሁለት አመት ግድም ቀይ ባሕር የተፈጠፈጠ አዉሮፕላን አደጋ ነበረ።ዘንድሮ የጨርቃጨርቅ ሠራተኞች አድማ አለ።የካይሮ ድሆች የሚኖሩበት አካባቢ ከፍተኛ የዉሐ እጥረት አለ።

እነዚሕና ብጤዎቻቸዉ ሐቆች መንግሥት ለሚቆጣጠሯቸዉ መገናኛ ዘዴዎች ብዙም ሐቅ አይደሉም።እና ከሕዝብ አይን አድራሾቹ ሐቅና ብጤዎቹ ናቸዉ።በዚሕም ሰበብ የጋዜጠኛ ወኢል ኢብሪሽ ዝግጅትን ብዙ ተመልካች የሚወደዉን ያሕል መንግሥት ይጠለዋል።እና ከእንግዲሕ የግብፁ ማስታወቂያ ሚንስትር አነስ ፈቂሕ እንደሚሉት ሐቅንና ብጤዎቹን የሚታገሳቸዉ የለም።

«የአረብ ሊግ ማስታወቂያ ሚንስትሮች እየተስፋፋ የመጣዉ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥር በሙያዉ ያልሰለጠኑ ሰዎች መጠራቀሚያ ሲሆኑ ዝም ብለዉ የሚያዩበት ትዕግስት የላቸዉም።አንዳዶቹ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የአረብን ማሕበረሰብ ለማወክና ነባር ይትባሐሉን ለማመሰቃቀል መሳሪያና ችግር ፈጣሪነታቸዉ መቆም አለበት።»

የአረብ ሊግ አባል ሐገራት ማስታወቂያ ሚንስትሮች ባፀደቁት ደንብ መሠረት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የማሕበረሰቡን ፍቅር፣ ብሄራዊ አንድነቱን፣ የሕግ ሥርዓቱን፣ እና ባሕላዊና ሐይማኖታዊ እሴቱን የሚያጎድፉ ዘገባዎች ማሰራጨት የለባቸዉም።ከሁሉም በላይ መሪዎችን የሚጎዳ፣ ብሔራዊና ሐይማኖታዊ ደንቦችን ማራከስ የለባቸዉም።እነሱ ማናቸዉና-ይጠይቃል?-ይጠይቃል ኢብሪሽ።

«ቴሌቪዥን ጣቢያ በነዚሕ በማያፈናፍኑ ቃላትና ደንቦች መሠረት ይሠራት ማላት ዘበት።የአንድ ማሕበረሰብ መሠረታዊ ወጎችና ደንቦች መኖራቸዉ አያጠያይቅም።ይሕን ማንም ያዉቀዋል።የወጎቹን ማንነትና ምንነት የሚበይነዉ ግን-ማነዉ?ወይስ የአረቡ አለም ፖለቲከኞችን መተቸት አይቻልም ማለት ነዉ? እንዲሕ አይነቱን አስተሳሰብ ዘመን ያለፈበት ነዉ።ደንቡ ከዮሴፍ ገብል (የሒትለር ማስታወቂያ ሚንስትር) መርሕ ጋር ይመሳሰልብኛል።ወይም በ1960ዎቹ ግብፅ ትከተለዉ የነበረዉን ሶሻሊስታዊ የመገናኛ ዘዴ አሠራርን ያስታዉሰኛል።(የደንቡ አዉጪዎች ደንቡ) ማሕበረሰቡን ለመደገፍ እና ነፃነትን ለማረጋገጥ ማለሙን ይናገራሉ በተጨባጭ ግን ፖለቲካዊ ሥርዓቱን የሚያጠናክር ነዉ።»


ጋዜጠኛ ኢብሪሽ ዝግጅቱ አይደለም እሱ እራሱ እንዲሕ እየተናገረ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነዉ።የግብፁን ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክን የሚተች ዘገባ በመፃፉ «የሐሰት መረጃ ማሰራጨት»በሚል ወንጀል ተከሷል።ዘብጥያ-አለያም የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል።እስከዚያዉ ግን ይናገራል።

«ባለሥልጣናት የተቃዉሞ ሠልፎችን ወይም ሥራ ያቆሙ አድማኞችን መሥል በየቴሌቪዥኑ ማየት አለመፈለጋቸዉን የሚያጋግጥ ነዉ።የሳተላይት ቴሌቪን ሥርጭት መስፋፋት ሕዝቡ የሚያነሳዉ የመብት ጥያቄ እየተበራከተዉ እንደ ሆነ አንድ ባለሥልጣን በግልፅ ነግረዉኛል።ይሕን ይፈሩታል።በቴሌቪን ጣቢያዉ የሚሰራጩት ፖለቲካዊ ዝግጅቶች ለሕዝቡ መብቱ እያሳወቁ፤ መብቱን ለማስከበር የሚያደርገዉን ትግል እያጠናከሩት ነዉ።መንግሥት ደግሞ ይሕ በሕዝቡ ዘንድ እንዲሰርፅ መንግሥት አይፈልግም።

ደንቡን ያረቀቁት፣ ሊጉ እንዲያፀድቀዉ የገፋፋትም ግብፅና ስዑዲ አረቢያ ናቸዉ።ከሃያ ሁለት አባል ሐገራት ማስታወቂያ ሚንስትሮች ደንቡን የተቃወሙት የቀጠሩ ሚንስትር ብቻ ናቸዉ።ቀጠር በአለም በተለይ በአረቡ አለም የመገናኛ ዘዴዎች ታሪክ ትልቅ አብዮት የጀመረዉ የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ርዕሠ-መንበር።