የአረብ ሊግ ና ለውጡ | ዓለም | DW | 28.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአረብ ሊግ ና ለውጡ

የአረብ መንግሥታት ማህበር አባል ሃገራት ጉባኤ ነገ ባግዳድ ኢራቅ ውስጥ ይካሄዳል። በዋዜማዛሬ የሊጉየውጭጉዳይሚኒስትሮችየሶሪያውን ብጥብጥ ለማስቆም በመፍትሄነት በተረቀቀው የውሳኔ ሃሳብ ላይ መክረዋል ። ኢራቅ ይህንመሰሉን ጉባኤ ስታሰተናግድ


ካለፉት20 የአረብ መንግሥታት ማህበር አባል ሃገራት ጉባኤ ነገ ባግዳድ ኢራቅ ውስጥ ይካሄዳል። በዋዜማዛሬ የሊጉየውጭጉዳይሚኒስትሮችየሶሪያውን ብጥብጥ ለማስቆም በመፍትሄነት በተረቀቀው የውሳኔ ሃሳብ ላይ መክረዋል ። ኢራቅ ይህንመሰሉን ጉባኤ ስታሰተናግድ ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያው በመሆኑ ጉባኤውን በዓይነቱ የተለየ ያደርገዋል። ጉባኤውን መነሻ በማድረግ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአቋም ለውጥ የሚታይበትን የአረብ ሊግ ይዞታ የዶቼቬለው Nils Naumann ቃኝቶታል ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች።

የአረብ መንግሥታት ማህበር የቀድሞዎቹን የሊቢያውን መሬ ሞአመር ጋዳፊን የግብጹን ሆስኒ ሙባረክን የቱኒዝያውን ዚኒ ኤል አቢዲን ቤን አሊን የመሳሰሉ አምባገነኖችን ይዞ የዘለቀ ማህበር ነበር ። በአፍሪቃና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አረብኛ ተናጋሪ ህዝቦች ያሏቿውን 22 ሃገራት ባሰባሰበው በዚህ ማህበርየ አባላቱ ፖለቲካዊ ግትርነት ይንፀባርቃል። ማህበሩ ጉባኤውን ባካሄደቁ ጥር ተመሳሳይ መግለጫ በማውጣት ነውየሚጠናቀቀው። ማህበሩን በአካባቢው

Arabische Liga Flagge

የማህበሩ ባንዲራ

ሃገራት ህዝቦችም ይሁን በምሥራቅና በምዕራብ ዓለም ፖለቲከኞች ዘንድ በቁም ነገር የሚያየውየለም። በዚህ ላይ ደግሞ በአረቡ ዓለም የተፈጠረው የለውጥ ንቅናቄ ሁኔታዎችን ለውጧል። አሁን የአረብ መንግሥታት ማህበር አዲስ መልክ የያዘ ይመስላል ። ለውጡ የተጀመረው እጎእ በ2011 መጀመሪያ ላይነ ው። ያኔ ማህበሩ የሊቢያውን አምባገነን መሪ ሞአመር ጋዳፊን በመቃወም ሊቢያን ከአባልነት አግዶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ደገፈ። ማህበሩ ካለፈው ህዳር አንስቶም ሶሪያ በማንኛውም ስብሰባ እንዳትካፈል ከልክሏል።

Ägyptens Außenminister Al-Arabi Generalsekretär der Arabischen Liga

ናቢል አል አረቢያ የማህበሩ ዋና ፀሃፊ

ከ2 ሳምንታት በኋላም በአረቡማህበረሰብ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሶሪያ ላያ ማዕቀብ ጣለ። በይፋ የሚነገረውየአረብ መንግሥታት ማህበር ዋናው ትኩረት ዲሞክራሲን ማስፋፋትና ሰብዓዊ መብቶችን ማስጠበቅ ነው ። ከበስተጀርባው ግን ያለው ሃቅ ሰፋ ያለ አካባቢያዊና ምልክአ ምድራዊ ይዞታያላቸውፖለቲካዊ ጥቅሞች ናቸው።ይላሉ በበ ነፃው የበርሊን ዩኒቨርስቲ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች አጥኚና ፕሮፌሰር ሃማዲ ኤል አዉኒ

« ማህበሩ ሁሌም የአካባቢው ትላልቅ አገራት ነፀብራቅ ነበር አሁንም ያው ነው ። ዛሪ ግን ተፅዕኖ የሚያደርጉት በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ያሉ በነዳጅ ዘይት የበለፀጉ ትናንሽ መንግሥታትና ሊቢያ ቱኒዝያ እና ግብፅ በቅርቡ ሥልጣን የያዙ እስላማዊ ንቅናቄ ኃይላት ናቸው ። »

በአሁኑ ጊዜ የአረብ ሊግ ዋንኛ አንቀሳቃሾች በተለይ ቃታርና ሳውዲ አረቢያ ናቸው ። በሊቢያው ህዝባዊ አመፅ ወቅት እንኳን ቃታር በሊቢያ ከበረራ ነፃ ክልልን ለማሰከበር በተካሄደው የአየር ድበደባ ተካፍላለች ። ይህ ደግሞ ኳታርና ሳውዲ አረቢያ ለዲሞክራሲ እንቆማለን ማለታቸውን ተአማኒነት ያሳጣዋል እንደ አዉኒ

« እነዚህ መንግሥታት ዲሞክራሲያዊ አይደሉም ። ፓርላማም የላቸውም ።ሰብዓዊ መብቶችም ያን ያህል ትኩረት አይሰጡም ። እነዚሁ ሃገራት በዓለም ዙሪያ ለዲሞክራሲ የቆሙ አገራት እንደሆኑ ተደርገው እንዲታመኑ ይፈልጋሉ ። ይህ ግን ተዓማኒነተ የለውም »

በዙሪክ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ኤልሃማ ማንያም ተመሳሳይ አስተያየት ነው ያላቸው ። በማንያ እምነት ስዑዲ አረብያና ቃታር በማህበሩ ውስጥ የግል ጥቅማቸውን ነው የሚያራምዱት ።

Syrien Arabische Liga

« ህዝቡ ሊደመጥ ይገባል የሚሉ የህዝብን መብት ዓርማ ያነገቡ ነገር ግን ጭርሱኑ ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑትን ሁለቱ አገራት ሳውዲ አረቢያ እጠርን እናገኛለን ። በሌላ በኩል ሳውዲ አረቢያ በምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙትን ሺአዎች እንዴት እንደያዘቻቸው እናያለን ። የተዓማኒነት ችግር እንዳለ እንገነዘባለን ። ስዑዲና ቃታር ይህን ፖለቲካ ለትክክለኛ ምክንያት አየተጠቀሙበት አይደለም ፤ ለራሳቸው ጥቅም እንጂ ። »

የ2 ቱ አገራት ዋና ግብ ዲሞክራሲን ማስፋፋት ሳይሆን ተቀናቃኛቸውን ኢራንን ማዳከም ነው እንደ ትንታኟ ። የኢራን መዳከምና የፋርስ ባህረ ሠላጤ ሃገራት መጠናከር ደግሞ የምዕራባውያን ሃገራትም ፍላጎት ነው እንደ ሃማዲ ኢል አወኒ ። በአዉኒ እምነት ማህበሩ በአካባቢው የምዕራባውያንን ፍላጎት ማሰጠበቁን ህጋዊ ለማድረግ እንደ መሣሪያ እያገለገለ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 28.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14TdU

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 28.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14TdU