1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረብና እስልምና ዕምነት ተከታይ አገሮች መሪዎች የጋራ ጉባኤ ምን መከረ?

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 3 2017

የአረብ ሊግና የእስላም አገሮች ትብብር የጋራ ጉባኤ ትናንት በሳኡዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሂዶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። በሳኡዲ አረቢያ የተጠራውና የተስተናገደው ይህ ጉባኤ 57 የአረብና ሌሎች የእስልምና እምነት ተክታያ አገሮች መሪዎች ተካፍለዉበታል።

https://p.dw.com/p/4mvfO
Saudi-Arabien Riad 2024 | Erdogan beim Sondergipfel von OIC und Arabischer Liga
ምስል Turkish Presidency/Murat Kula/Anadolu/picture alliance

የአረብ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ እና የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ

የአረብና እስልምና ዕምነት ተከታይ አገሮች መሪዎች የጋራ ጉባኤ አጀንዳ

የአረብ ሊግና የእስላም አገሮች ትብብር የጋራ ጉባኤ ትናንት በሳኡዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሂዶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። በሳኡዲ አረቢያ የተጠራውና የተስተናገደው  ይህ ጉባኤ 57 የአረብና ሌሎች የእስልምና እምነት ተክታያ አገሮች መሪዎች የተካፈሉበት ሲሆን፤  ዋና አጀንዳውም የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታና በተለይም እስራኤል በፍልስጤም ህዝብ ላይና  በሊባኖስ እየፈጽመችው ያለው ጥቃትና ወንጀል መሆኑ ተገልጿል።

በጉባኤው የተሰሙ ውግዘቶች፤ ወቀሳዎች፤ የተደረጉ ጥሪዎች

የአስተንጋጁዋ አገር ሳኡዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር እስራኤልን በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰዋል፣ የዓለማቀፉ ማህበረሰብም እስራኤል በጋዛና ሊባኖስ እያደረሰች ያለውን ጥቃት ማስቆም ባለመቻሉ ወቅሰዋል። ጦርነቱ  ባስቸኳይ እንዲቆምና የፍልስጤም ህዝብ ችግርም በዘላቂነት እንዲፈታ ጠይቀዋል። የቱርኩ ፕሬዝድዳናት ሚስተር ኢርዶጋንም፤ እስራኤል በጋዛና ሊባኖስ የጦር ወንጀል እየፈጽመች መሆኑን በማንሳት፤ እሳቸውም አለማቀፉ ማህብረሰብ ኢስራኤልን ከእንደዚህ አይነት ኢሰባዊ ድርጊትና የጦር ወንጀል እንድትቆጠብ ተገቢና በቂ እርምጃ ባለመውሰዱ ወቅሰዋል። የአረብና እስላማዊ አገሮችም በፍልስጠኤም ህዝብና በሊባኖስ ላይ እየተፈጸመ  ያለው ወታደራዊ ጥቃት፣ እየደረሰ ያለው ሰባዊ ቀውስና እረህብ ኤንዲቆም የሚጠበቅባቸውን  አለማድረጋቸን በመጥቀስም በጋራ በመቆምና በመተባበር እስራኤል የምታደርሰውን ጥቃት ማስቆም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የአረብ ሊግ አባል ሐገራት የሶሪያን አባልነት በይፋ አፀደቁ

ጉባኤው የተካሂደበት ድባብና ተጠባቂ ውጤቶች

ተመሳሳይ ጉባኤ ባለፈው አመት በሪያድ ተጠርቶ የነበር ሲሆን፤ የአሁኑ ጉባኤ ግን ኢስራኤል በጋዛ ብቻ ሳይሆን በሊባኖስም ጦርነት በከፈተችበትና ከየመን ሁቲ ታጣቂዎችና ከኢራን ጋርም መታኮስ በጅመረችበት፤ የፍልስጤምም ህዝብ ችግርም እጅግ የከፋ በሆነበት ወቅት ነው።  ጉባኤው በጋዛና ሊባኖስ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግና ለፍልስጤምም ህዝብ ችግርም ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ታልሞ የተጠራ እንደሆነ ቢነገርም፤ ተጨጫጭ ውጤት ማስገኘቱን ግን ብዙዎች ይጠራጠራሉ።

የአረብ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ
የአስተንጋጁዋ አገር ሳኡዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር እስራኤልን በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰዋልምስል Turkish Presidency/Murat Kula/Anadolu/picture alliance

የአውሮጳ ኅብረት እና የአረብ ሊግ ጉባኤ 

የጉባኤው ተሳታፊ አገራት አንድነትና ልዩነት

 የጉባኤው ተስታፊ አገራት በፍልስጤም ችግርና በመካከለኛው ምስራቅ  ሁኔታ ላይ የጋር ግንዛቤና አቋም የሌላቸው መሆኑ በእስራኤል ላይ የጋራና ጠንካራ አቋም እንዳይወስዱ እንዳደረጋቸው ነው የሚታመነው።  የፍልስጤም ብሄራዊ ኢንሸቲቭ  ዋና ጸሀፊ ሙስተፋ ባርግሁቲ፤ እነዚህ አገሮች የፍልስጤምን ህዝብ ጥያቄ በመደገፍ በእስራኤል አንጻር በአንድነት ሊቆሙ ያልቻሉባቸውን ምክኒያቶች ይዘርዝራ፤ “ ለዚህ ምክኒያቱ እንደሚመስለኝ አንዳንዶቹ አገሮች እርምጃ ለመውሰድ ስለሜፈሩ ነው፡፤ ሌሎቹ ደግሞ ከአሜሪካ  ጋር ያለቸው ግንኙነት እንዲበላሽ ስለማይፈልጉ ነው። ከእስራኤል ጋር የመሰረቱት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት  እንዳይበላሽ የሚፍልጉም አሉ፤” በማለት እስራኤል ግን  በሁኑ ወቅት የሁለት አገሮች የመፍትሄ ሀሳብን ውድቅ ያደረገች በመሆኑ የሚያዋጣው ሁሉም የአረብና እስላም አገሮች ኢስራኤልን ቢያገሉና ማእቀብ ቢጥሉባት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የሻርም ኤልሼኩ የአውሮጳ እና የአረብ ሊግ ጉባኤ

የጉባኤው መግለጫ ይዘት

ከአረብና እስላምዊ አገሮች ስብስብ ሳኡዲ አረቢያ፣ የተባበሩት ኢሜሪት፤ ካታር ባህሬን፣ ግብጽን ሞሮኮ በአሜሪካ አቀራርሪቢነት ከእስራኤል ጋር ዲፖሎማሲያዊ ግንኑነት እንደመሰረቱ ነው የሚነገረው። ባንጻሩ ኢራን፣ ሶሪያና አልጀሪያ የመሳሰሉት ደግሞ ከእስራኤል ጋር አንድም በጦር ይፈላለጋሉ ወይንም ወዳጅነት የላቸውም። በዚህ ጉባኤ ግን ሁሉም እስራኤልን ባማውገዝ ባስቸኳይ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግና በሁለት አገሮች የመፍትሄ ሀሳብ መሰረት የፍልስጠም ነጻነት እንዲረጋገጥ ባጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የፍልስጤም መርጃ ድርጅት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳና ሰባዊ እርዳታ እንዴደርስም አጥብቀው ጠይቀዋል።

የአረብ ሊግ ጥምር ጦር ለማቋቋም አሰበ

ተመራጩ የእሜሪካ ፕሬዝዳንት ምን ያደርጉ ይሆን?

ባንድ በኩል ጦርነቱ እንዲቆም እየጠየቀች ግን የጦር መሳሪያ ስታቀብል የቆየችው የፕሬዝዳንት ባይደን አሜሪካ  አሁን ዳግም ወደስልጣን በመጢት ፕሬዝዳንት ትርራምፕ ስር ስትሆን የምታደርገው በትክክል አይታወቅም። ፕሬዝዳንት ትራም የፍልስጤምን ጥያቄ ማዳፈን የምተፍልገውን እስራኤልን ይደግፋሉ ቢባልም፤ የጋዛን ጦርነት ግን እንደሚያስቆሙ ሲናገሩ ተሰምተዋል። እሳቸው የሳኡዲ አረቢያና ሌሎች የገልፍ ባህረሰላጤ አገሮችም ወዳጅ በመሆናቸውም በሚስተር ናታኒያሁ መንግስት ላይ ጭና በማሳደር ምናልባትም ሌሎች ሊያመጡ ያልቻሉትን ሰላም ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል የሚሉም አሉ።

የጉባኤው ተሳታፊ የአረብ ሃገራት
የፕሬዝዳንት ባይደን አሜሪካ  አሁን ዳግም ወደስልጣን በመጢት ፕሬዝዳንት ትርራምፕ ስር ስትሆን የምታደርገው በትክክል አይታወቅም። ምስል Saudi Press Agency/Handout/REUTERS

የፍልስጤም ብሄራዊ ኢኒሸቲቭ ዋና ጸሀፊው ሚስተር ሙስተፋ፤ የአረብና የእስልምና እመንት ተክታይ አገሮች ከተባበሩ  ፕሬዝድንት ትራምፕን ሊይሳምኑ የሚችሉባቸው ዘዴዎች አሉ፤ “ በርክታ ስልቶችና ዘዴዎች አሉ። አንደኛው እስራኤል እየፈጸመች ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እስካላቆመች ድረስ በየአገሮቻቸው ያሉ የጦር ሰፈሮቿን እንዳትጠቀም መከልከል ነው። ሁለተኛው ምርቶቿን አለመግዛት ነው ። ሶተኛው አሜርካንን በየትኛም አለማቀፍ መድረክ እንደማይደግፉ ማሳወቅ ነው፤ ሌላው ደግሞ ሁሉም ከእስራኤል ጋር የመሰረቱትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረዝና  ማዕቀብ መጣል ነው በማለት በርካታ አሳማኝና አስገዳጅ ዘዴዎች ያሉ መሆኑን ገልጸዋል

ገበያው ንጉሤ

ለዲደብሊው

ብራስልስ