የአረቡ ዓለም የህዝበ አመጽ እስራኤልና የአውሮፓ ህብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአረቡ ዓለም የህዝበ አመጽ እስራኤልና የአውሮፓ ህብረት

በዓረቡ ዓለም የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ በአጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ አገራትና በተለይ በእስራኤልም ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ አያጠያይቅም ።

default

አቪድጎር ሊበርማን

በሰሜን አፍሪቃ እና በመካከለኛው ምስራቅ ለዘመናት አምባገንን ሆነው የዘለቁ መሪዎችን ማስወገጃ እና የፍትህ እና የዲሞክራሲ ማስፈኛ አቋራጭ መንገድ ተደርጎ የተወሰደው የዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ ውጤት በተቃራኒው ይሆናል ከሚል ስጋት ጋር ነው እስራኤል የምታየው ። ከእስራኤል ስጋት አንዱ አመፁ ፣ የሚፈለገውንና የሚጠበቀውን ዲሞክራሲ ከማምጣት ይልቅ በየሀገራቱ አክራሪ ሙስሊም መንግስታት እንዲፈጠሩ ያደርጋል የሚል ነው ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቪድጎር ሊበርማን ከአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ብራሰልስ ውስጥ የመከሩባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች ይመለከታል ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ