የአምደ መረብ እገዳን ለመቋቋም DW እና Psiphonን መጠቀም | ኢትዮጵያ | DW | 18.06.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአምደ መረብ እገዳን ለመቋቋም DW እና Psiphonን መጠቀም

መንግስታት በአምደ መረብ ላይ የሚያደርጉት ቅድመ ምርመራ፣ እገዳ ወይም ሳንሱር ሐሳብን በነፃ የመግለፅ መብትን የሚያሰጋ ነዉ። ይሕን እገዳ ለመቋቋም፣ ዶይቸ ቬለ (DW) እ.ጎ.አ. ከ 2012 አንስቶ Psiphon የተባለዉን መሣሪያ በመጠቀም የራሱንና ተመሳሳይ እገዳ የሚያርፍባቸዉን ሌሎች ገፆች ለአንባቢ-አድማጭ እንዲደርሱ ያስችላል።

ከ DW ዋና ዋና ተልዕኮዎች አንዱ ሀሳብን በነፃነት መግለፅና መረጃን በመላዉ ዓለም በነፃ የማግኘት ፍላጎትን ማሟላት ነው።በአምደ መረብ ላይ የሚደረጉ ቅድመ ምርመራዎች ወይም እገዳዎች ግን  ይህ እንዳይሆን ሥጋት እየፈጠሩ ነው። እንደ DW ያሉ አስተማማኝ መረጃዎችን የሚያሰራጩና  የሚያወያዩ  የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መድረኮችን የሚያዘጋጁ የዜና አዉታሮችን የሚያግዱ መንግስታት ቁጥር እየጨመረ ነው።

እገዳ የሚጥሉ መንግስታት በሚመሯቸዉ ሐገራት የሚኖረዉ ተጠቃሚ የDWና የሌሎች መገናኛ ዘዴዎችን የታገዱ መረጃዎችን እንዲያገኙ DW የመገናኛ ዘዴ ነፃነትን ለመጠበቅ፣psiphon  ከተሰኘዉ የካናዳ የንግድ ድርጅት ጋር በመተባበር እገዳ ወይም ሳንሱርን ማለፊያ መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል።

Psiphon የተለያዩ እገዳ ማስወገጃ ብልሐቶች ያሉት መተግበሪያዎችን (አፕሊኬሽንስ) እና የኮምፒዉተር ፕሮግራሞችን ፣ proxy እና VPN የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን ያቀርባል።DW እገዳ የተደረገበትን መረጃን ለተከታታዮች ለማድረስ  የተለያዩ የ Psiphon ቴክኖሎጂ አማራጮችን ይጠቀማል።

የታገደ የDW መረጃን በ DW መተግበሪያ የማግኛ ዘዴ

እ.ጎ.አ. ከ 2020 ጀምሮ የ Psiphon ሶፍትዌር ለIOSና ለAndroid በተዘጋጁ የ DW መተግበሪያዎች ላይ ተቀናብሯል። ይህም ዝቅተኛ ወይም ውስን የአምደ መረብ አገልግሎት ባላቸው ሐገራት የDW መረጃ  እንዲደርስ ይረዳል። ለምሳሌ የDW መረጃዎች በተዘጉባቸው ኢራንና ቻይና የሚገኙ ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ «proxy» የተባለውን መገልገያ በመጠቀም የ DW መረጃን ያገኛሉ።

ይህንን ለማድረግ በ DW መተግበሪያ አናት  በግራ በኩል ያለውን ምልዕክት (ሶስት መስመሮች) ላይ ይጫኑ «ጠቅ» ያድርጉ ፣ከዛም  “PROXY” የሚለውን ይጫኑ፤ በመጨረሻም "Activate Proxy"  የሚለውን ይጫኑ (ምስሉን ይመልከቱ)።

ማሳሰቢያ፦ፕሮክሲ በማውረጃ (ዳውንሎድ) ፍጥነት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚጠቀም ያስተዉሉ። ከዚህም ሌላ፣ ፕሮክሲ መጠቀም በአንዳድ ሐገራት ሕገ ወጥ ሊሆን ይችላል።

ለመጠቀም ከወሰኑ ግን የDW መተግበሪያን ከ Apple App Store (iOS) ወይም ከ Google Play Stor (Android) ማውረድ ይቻላል። 

የ DW መተግበሪያን ለማወረድ እዚሕ ይጫኑ

የDW Psiphon መተግበሪያን በመጠቀም ሌሎች የታገዱ ገፆችን ማግኘት

መንግስታት፣ ትዊተርና ፌስቡክን የመሳሰሉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና ድረ ገፆችን በማገድ ሰዎች  ሐሳባቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ የሚያደርጉት ጫና በጣም እየተዘወተረ ነዉ። ስለሆነም DW ከራሱ መተግበሪያ በተጨማሪ በሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ እና ሳንሱር የሚደረጉ መረጃዎችን መክፈት እንዲቻል ከ Psiphon ጋር እየሰራ ነዉ።

Infografik Censorship bypass app Psiphon download instructions

ገፁን ዳውንሎድ ማድረግ ከፈለጉ ባዶ ኢሜል በዚህ አድራሻ dw-w@psiphon3.com ይላኩ።

እንደዚህ አይነት ችግር ካጋጠምዎ Psiphon መተግበሪያን ለመጠቀም ያስቡበት። መተግበሪያውን (iOS / Android) ስልክዎ ወይም በዴስክቶፕ ላይ ለመጫን dw-w@psiphon3.com ላይ ኢሜል ይላኩ። በ DW በኩል Psiphon የሚጠቀሙ ከሆነ በመጀመሪያ ወደ DW ድረ ገፅ ይመራሉ (ይገባሉ)። ከዚያ ወደ ማናቸውም ሌሎች ገፆች መቀጠል ይችላሉ።