የአምደኛ ርዕዮት መሸለም | ዓለም | DW | 15.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአምደኛ ርዕዮት መሸለም

የድርጅቱ ምክትል ሐላፊ ኤሊዛ ሙኞዝ ድርጅታቸዉ ርዕዮትን ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ለዘንድሮ ሽልማት የመረጠበትን ምክንያት አስታከዉ እንዳሉት ርዕዮት ለእምነቷና ለጋዜጠኝነት ክብር ስትል ያላትን ሁሉ ሰዉታለች።

--- DW-Grafik: Per Sander 2010_11_24_symbolbild_pressefreiheit.psd

በእስር ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያዊቷ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ ለጋዜጠኝነት ሙያ በቁርጠኝነት መቆሟን የዓለም ሴት፥ የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ምክትል ሐላፊ ኤሊዛ ሙኞዝ ድርጅታቸዉ ርዕዮትን ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ለዘንድሮ ሽልማት የመረጠበትን ምክንያት አስታከዉ እንዳሉት ርዕዮት ለእምነቷና ለጋዜጠኝነት ክብር ስትል ያላትን ሁሉ ሰዉታለች። የሰላሳ አንድ አመቷ መምሕርትና የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በአሸባሪነት ተወንጀላ የአስራ-አራት አመት እስራትና የሰላሳ ሺሕ ብር ቅጣት ተበይኖባት ታስራለች።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic