የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ | ዓለም | DW | 24.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ

የፖለቲካ ለውጥ ለማስገኘት ሲባል አደባባይ መውጣት ድፍረትን ይጠይቃል። በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያንም ይህ ድፍረት እንዳላቸው ባለፈው ዓመት አስመስክረዋል። በሰሜን አፍሪቃ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ብቻ ሳይሆን ፡ ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉት አፍሪቃውያት ሀገሮችም እጅግ ብዙ ሕዝብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት አንጻር አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምቶዋል።

ይኸው በሰሜን አፍሪቃ የተነቃቃውና ወደ ሌሎች የአፍሪቃ አካባቢዎች የተዛመተው ዓብዮት ግን ሕዝቦች የጠበቁትን ጥሩ ውጤት እንዳላስገኘላቸው በያመቱ በዓለም ያለውን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የሚመረምረው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘንድሮ ያወጣው ዘገባ አመልክቶዋል።

በሴኔጋል መዲና ዳካር ባለፈው  31.01. 2012 ብርቱ ተቃውሞ ነበር የተካሄደው። በሴኔጋል እንደሆነው ባለፉት አሥራ ሁለት ወራት የሌሎች በርካታ አፍሪቃውያት ሀገሮች ከተሞችም መንገዶች የተቃውሞ ቦታዎች እንደነበሩ የእነስቲ የአፍሪቃ ክፍል ዳይሬክተር ኤርቪም ፋን ደር ቦርት አስታውቀዋል።
«ገዢዎቹ የወሰዱት ርምጃ አዘውትሮ ጠንካራ መሆኑ ነው ችግሩ። ተቃውሞ ሰልፎችን ደምስሰዋል። ብዙ ጊዜም በፖሊስ ኃይል በመጠቀም መደምሰሳቸእ ለበምሳሌነት ይጠቀሳል። በብዙ ከአፍሪቃ በስተደቡብ የሚገኙት የብዙዎቹ ገዢዎች ርምጃ በጣም ቅር የሚያስኝ ነው። ተጨማሪ ነፃነት እንዲኖር፡ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖር፡ በድህነት አንፃር ትግል እንድደረግ ለቀረቡት ጥያቄዎች አዎንታዊ  መልስ በመስጠት እና ችግሩ መኖሩን አውቀው በመቀበል  ፈንታ ተቃውሞውንና ተቃዋሚዎችን በኃይል ርምጃ  ደምስሰዋል። »
በሱዳን፡ ይሁን በአንጎላ፡ በዚምባብዌ ወይም በሴኔጋል የታዩት ተቃውሞዎች በፀጥታ ኃይላት ርምጃ ተበትነዋል። የሞተና የቆሰለም ነበር። ፋን ደር ቦርት
« ከሰሀራ በስተደቡብ የሚገኙት የብዙዎቹ አፍሪቃውያት ሀገሮች የፖለቲካ መሪዎች ከመፍትሔው ይልቅ የችግሩ አካል ነበሩ። »

sday, May 11, 2011. Besigye was kicked off a flight from Kenya on Wednesday, prompting riots back home that police quelled with tear gas only a day before the country's president of 25 years was due to be sworn in for another term. (AP Photo/Khalil Senosi)

ኪዛ ቢሲጄይ


ለምሳሌ የዩጋንዳ መንግሥት ባለፈው ዓመት የካቲት ወር በሀገሩ ምርጫ በተካሄደበት ወቅት ተቃውሞ ሰልፍ እንዳይደረግ ከልክሎ ነበር። ይህን የመንግሥት ርምጃ እንደ ችግር ያላየው አክቲቪስትስ ፎር ቸንጅ የተሰኘው የተቃዋሚ ወገኖች ህብረት ሕዝቡ በውዱ የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ፡ እንዲሁም፡ የፕሬስ ነፃነት የታፈነበትን አሰራር በመቃወም ወደ ሥራ ቦታው በእግሩ እንዲጓዝ ጥሪ አቀረበ፤ በዚሁ ጥሪ መሠረትም፡ በመዲናይቱ ካምፓላና በሌሎች ትልቆችቹ ከተሞች ለብዙ ሣምንታት ተቃውሞ በመቀጠሉ ፖሊስ የተቃዋሚ ወገኖች ጠንካራ ሰፈሮች ያላቸውን ቦታዎች ውኃ እና ቀይ ቀለም በመርጨት አፀፋ ርምጃ ወስዶዋል። ይህንኑ የመንግሥቱ ርምጃ ዋነኛው የተቃዋሚ ወገን መሪ ኪዛ ቢሲጄይ እንደ ፍርሀት ነው የተመለከቱት።
« መንግሥት ፈርቶዋል። እኔ ወደ ሥራ ቦታዬ በእግሬ በመጓዜ ምክንያት አይደለም የፈራው። የፈራው የራሱን ዜጎች ነው። »

የአምነስቲ ዘገባ አሳሳቢ ያለው ሌላው ጉዳይ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል የቀጠለው ውዝግብ ነው። ደቡብ ሱዳን እአአ ባለፈው ዓመት ሀምሌ ወር በሰላማዊ መንገድ ነፃነትዋን ብታገኝም በሁለቱ ሱዳን መንግሥታት መካከል በነዳጅ ዘይት የታደለው በድንበሩ አካባቢ የሚገኘው የአቢየ ጥያቄ፡ በሱዳን የብሉ ናይል እና በደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች የተፈጠረው ውዝግብ እና በደቡብ ሱዳን የሚታየው የጎሳ ግጭት መልስ ባለማግኘቱ፡ ባካባቢው የሰብዓዊ ቀዋስ ተፈጥሮ፡ ግድያና ክትትል መስፋፋቱን የአምነስቲ የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ኤርቪን ፋን ደር ቦርት ገልጸዋል።

Photo: Abandoned hut in Abyei, Verlassene Hütte in Abyei Description: Small abandoned hut in Abyei, Southern Sudan/ Die Bewohner dieser Hütte sind aus ihrem Dorf in Abyei , Süd Sudan, geflohen. Stichworte: Sudan, Süd Sudan, Guerilla, bewaffnet, Überfall, Dorf, Flüchtlinge, Abyei Date: March, 2011 Location: Abyei, Southern Sudan Photo credit: Guy Degen Photographer contact: guy.degen@dw-world.de

አቢዬ


« ችግሩ በሱዳን መንግሥት ብቻ ሳይሆን በደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናትም በኩል የሚታየው ክሽፈት ነው። ሁለቱም ወገኖች ከሕዝበ ውሳኔው በኋላና ከደቡብ ሱዳን ነፃነት በፊት፡ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ገቢ ክፍፍልን፡ የድንበር ማካለሉን፡ በየሀገሮቻቸው ያሉትን የሌላውን ሀገር የዜግነትንና የአቢየን ጥያቄ ለመሳሰሉት ዋነኞቹ አወዛጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ሳያስገኙ በመቅረታቸው ውጥረቱ እንዲካረርና ባለፈው ሚያዝያም ግልጹ ውዝግብ እንዲነሳ ምክንያት ሆኖዋል። »

Protesters take to the streets in Bamako, Mali, Monday May 21, 2012. They were protesting Dioncounda Traore's nomination to transitional president for the next 12 months. The junta led by Capt. Amadou Sanogo had been opposed to the extension of the interim president's term, which under the Malian constitution was due to run out on Tuesday. ECOWAS had threatened to reimpose sanctions on Mali if the junta did not stop interfering in the transition. (Foto:Harouna Traore/AP/dapd)

ተቃውሞ በማሊ


በማሊም ካለፉት ስድስት ሣምንታት ወዲህ በቀጠለው ውዝግብ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየከፋ መምጣቱን የአምነስቲ ዘገባ አመልክቶዋል። በጎረቤት ሊቢያ የቀድሞው መንግሥት ከተገረሰሰ በኋላ በዚያ የነበሩት የሙአመር ጋዳፊ ደጋፊ ተዋጊዎች ወደትውልድ ሀገራቸው ማሊ የተመለሱበት ድርጊት በሀገሪቱ ትልቅ ያለመረጋጋት ሁኔታ ፈጥሮ፡ በሰሜናዊ ማሊ በመንግሥቱ አንፃር የሚዋጉት የቱዋሬግ ዓማፅያን እና የአልቓይዳ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር ሰበብ ሆኖዋል። የሀገሩ መንግሥት በዚህ ሁኔታ አንፃር ተገቢውን ርምጃ አልወሰደም በሚል የጦር ኃይሉ አባላት መፈንቅለ መንግሥት ካካሄደበት ጊዜ ወዲህ በማሊ ብርቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መቀጠሉን ፋን ደር ቦርት አስታውቀዋል።
« በማሊ ሁኔታዎች እንዴት እንደሚቀጥሉ መናገር አዳጋች ነው።  አንዳንድ የጦር ኃይሉ አባላት በሀገር አመራሩ ላይ አሁንም በመዲናይቱ ባማኮ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ያለበት ሁኔታ አሳስቦናል። ይህ ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያስከትል ይችል ይሆናል። »
የሰብዓዊ መብቱ ተሟጋች ድርጅት ዘገባ ባለፈው ዓመት የአሸባሪዎች ጥቃት ቁጥር እየጨመረ የሄደበት ድርጊት አደገኛነትን አሳይቶዋል። በናይጀሪያ በሶማልያ እና በማግሬብ ሀገሮች የሚንቀሳቀሱት ቦኮ ሀራም ፡  አሸባብ  እና አክሚን የመሳሰሉት አክራሪ የሙስሊም ቡድኖች በጣሉዋቸው ጥቃቶች በተለይ ብዙ ሲቭል ሕዝብ ሰለባ ሆኖዋል። በዚህ ችእእእእግር አኳያ የሙስሊሞቹ ጥቃት የጣሉዋቸው ጥቃቶች ብቻ ሳይሆኑ፡ መየመንግሥት ጸጥታ ኃይላት የወሰዱት አጸፋ ርምጃም ችግሩን እንዳባባሰው ነው ያስታወቁት።
« በሽብርተኝነት ተግባር አንጻር መንግሥት እየፈጸመው ባለው አጸፋ ርምጃ መደዳ ለምሳሌ በጥቃቱ የተጠረጠሩ ሰዎች ይታሰራሉ ወይም በናይጀሪያ በተስፋፋ የእስራት ተግባር በመቶ የሚቆጠሩ ወህኒ ወርደዋል። በናይጀሪያ ብቻ ሳይሆን በሞሪታንያም  ሰዎች የት እንደደረሱ ሳይታወቅ እንደሚጠፉ፡ መታሰራቸው ሳይታወቅ እንደሚታሰሩ እና ባለስልጣናት መታሰራቸውን እንደሚያስተባብሉ አስተውለናል። ይህ ዓይነቱ ስጋት በተለይ ከሰሀራ በስተደቡብ በሚገኙት አፍሪቃውያት ሀገሮች ውስጥ በይበልጥ እየጎላ መጥቶዋል። »

ሽቴፋኒ ዱክሽታይን

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 24.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/151wJ
 • ቀን 24.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/151wJ