የአምነስቲ ማሳሰቢያ | ኢትዮጵያ | DW | 22.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአምነስቲ ማሳሰቢያ

አምነስቲ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ  የሚካሄደውን ለውጥ አድንቆ ፣ አሳሳቢ ያለው የኢትዮጵያ  የሰብዓዊ መብት አያያዝ  ግን ይበልጥ ሊሻሻል እንደሚገባ አሳስቧል። ከበፊቱ የተሻለ ነው ሲል የገለጸው አዲሱ የሲቪል ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ የተወሰኑ አንቀጾችም አሁንም ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:18

የአምነስቲ ጥሪ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይበልጥ እንዲሻሻል ጠየቀ። አምነስቲ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥሪ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ  በወሰዷቸው የለውጥ እርምጃዎች አድንቆ ፣ ሆኖም አሳሳቢ ያለው የኢትዮጵያ  የሰብዓዊ መብት አያያዝ  ይበልጥ ሊሻሻል እንደሚገባ አሳስቧል። ከበፊቱ የተሻለ ነው ሲል የገለጸው አዲሱ የሲቪል ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ የተወሰኑ አንቀጾችም አሁንም ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ያለውን ስጋት ገልጿል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት በበኩሉ አዲሱ  የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች አዋጅ ተገቢ ዝርዝር ጥናት የተደረገበት እና የማያሰራም እንዳልሆነ አስታውቋል። ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዘገባ አላት።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች