የአምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ሞት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

 የአምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ሞት

አምባሳደር ሽሚት በተለይ ከወጣቶች ጋር ስፖርትን በመሳሰሉ መስኮች በመገናኘት ወጣቶችን የሚደግፉና የሚያበረታቱ፤ የኢትዮጵያና የጀርመንን ግንኙነት ለማጠናከር አብክረዉ የጣሩ አምባሳደርም ነበሩ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:11

 የአምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ሞት

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት በማረፋቸዉ በቅርብ የሚያዉቋቸዉ ሐዘናቸዉን እየገለፁ ነዉ።አምባሳደር ሽሚት በጀርመን መንግሥትና ድርጅቶች የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን በየአካባቢዉ እየተዘዋወሩ በመጎብኘት፤ ለሕዝቡ የሚሰጡትን አገልግሎት በማበረታትና ከየማሕበረሰቡ ጋር በመወያየት የታወቁ ዲፕሎማት ነበሩ።አምባሳደር ሽሚት በተለይ ከወጣቶች ጋር ስፖርትን በመሳሰሉ መስኮች በመገናኘት ወጣቶችን የሚደግፉና የሚያበረታቱ፤ የኢትዮጵያና የጀርመንን ግንኙነት ለማጠናከር አብክረዉ የጣሩ አምባሳደርም ነበሩ።ሽሚት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2014 በኢትዮጵያ እና በአፍሪቃ ሕብረት የጀርመን አምባሳደር ሆነዉ ከመሾማቸዉ በፊት በቦስኒያ ሄርሶ ጎቪና እና በሰርቢያ የጀርመን አምባሳደር ሆነዉ አገልግለዋል።በሞታቸዉ የተነገረዉ ትናንት ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች