የ«አሜን ኢትዮጵያ» ድርጅት ጉባዔ  | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የ«አሜን ኢትዮጵያ» ድርጅት ጉባዔ 

በተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመሰረቱት አሜን ኢትዮጵያ የተባለው ድርጅት ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጉባዔ አካሄደ። ይኸው በኔዘርላንድስ የተቋቋመው ድርጅት በጉባዔው ያጎላው ዋና ነጥብ የመደማመጥ እና የመግባባት ባህልን በማዳበር ለልዩነቶች እና ለግጭቶች መፍትሔ ማስገኘት የሚለውን ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43

«የሌላውን ችግር በተቸገረው ሰው ዓይን መመልከት ይገባል።»

በጉባዔው የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና ስለሰላም ጥናት እና ምርምር ያደረጉ ምሁራን ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግቦ የሚሰራው ይኸው ድርጅት ጉባዔውን ያካሄደው የቀድሞው ፕሬዚደንት የመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለሰላም ስብሰባዎች በግቢያቸው ባሰሩት አዳራሽ ነበር። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic