የአሜሪካ ድጋፍ ለኢትዮጵያ | ዓለም | DW | 13.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካ ድጋፍ ለኢትዮጵያ

አንድ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ርዳታ የምትሰጠዉ ኢትዮጵያ ሠብአዊ መብትና ዴሞክራሲን ሥለምታከብር ሳይሆን ለፀጥታ ጥበቃ አስፈላጊ ሐገር በመሆንዋ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:31
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:31 ደቂቃ

የአሜሪካ ድጋፍ ለኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፤ ድርጅቶችና ተቋማት በየዓመቱ በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ድጋፍ እንደሚያገኝ ዘገቦች ጠቆሙ።የአሜሪካ መንግሥት የርዳታ ድርጅት USAID እንደዘገበዉ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2013 ብቻ ለኢትዮጵያ የ620 ሚሊዮን ዶላር የልማት ርዳታ ሰጥቷል።የቢል ጌትስና የክሊንተንን የመሳሰሉ ተቋማትም በጤናዉ ዘርፍ ከፍተኛ ርዳታ እየሰጡ ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከልማት ርዳታ በተጨማሪ ለወታደራዊና ለፀጥታም በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ድጋፍ ይሰጣል።አንድ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ርዳታ የምትሰጠዉ ኢትዮጵያ ሠብአዊ መብትና ዴሞክራሲን ሥለምታከብር ሳይሆን ለፀጥታ ጥበቃ አስፈላጊ ሐገር በመሆንዋ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል

ናትናኤል ወልዴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic