የአሜሪካ ድምፅና የኢትዮጵያ መንግሥት ውዝግብ | ዓለም | DW | 12.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካ ድምፅና የኢትዮጵያ መንግሥት ውዝግብ

የአሜሪካ ድምፅ (VOA) የአፍሪቃ ቀንድ የቋንቋዎች ክፍል ሐላፊ ዴቪድ አርኖልድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተደረገ ዉይይትን አላአግባብ አሠራጭተዋል በሚል ከሥራቸዉ ታግደዋል የሚለዉን ዘገባ ጣቢያዉ አስተባበለ።

default

ዴቪድ አርኖልድ የዩናይትድ ስቴትስ የማሰራጪያ ጣቢያ የገዢዎች ቦርድ የመልክተኞች ጓድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ጋር ባደረገዉ ዉይይት ላይ ተካፍለዉ ነበር። በዉይይቱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአሜሪካ ድምፅ ቃለ መጠይቅ እንዳይደረግላቸዉ ጠይቀዋል ያሏቸዉን ሰዎች ስም ዝርዝር አርኖልድ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛዉ አገልግሎት አሰራጭተዉ ነበር። ነጋሽ መሐመድ ሥለ ጉዳዩ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን አጋግሮታል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic