የአሜሪካ የህግ ረቂቅ መዘግየት | ዓለም | DW | 24.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካ የህግ ረቂቅ መዘግየት

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ጠንካራ ውሳኔ ለማስተላለፍ አቅዶ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡ ፍሪደም ሀውስ በመባል የሚታወቀው የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው የጽሁፍ መግለጫ የአሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ውሳኔውን ማራዘሙን ተቃውሟል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:49 ደቂቃ

የህግ ረቂቁን «በግፊት ማስቀረት አይቻልም» - ተሟጋቾች

የአሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ኤች አር 128 በሚል ስያሜ በተዘጋጀው በዚህ የህግ ረቂቅ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ ማራዘሙን ተቃውሟል፡፡ የህግ ረቂቁ የ71 የምክር ቤት አባላትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ በኮሚቴ ደረጃ በቀረበ ወቅት በሙሉ ድምጽ ማለፉን የሚያስታውሱ አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ባለሙያ በአሜሪካ በዚህ አይነት ሁኔታ ለምክር ቤት የቀረበን የህግ ረቂቅ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ባለ ግፊት ማስጣል እንደማይችል ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው፡፡

መክብብ ሸዋ
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic