1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካ እና እስራኤል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2009

«የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው » የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ።

https://p.dw.com/p/2V3aX
USA Außenminister John Kerry zu Lage in Nahost
ምስል Getty Images/Z. Gibson

Beri Wash.US-Israel clash - MP3-Stereo

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እስራኤል ምሥራቅ እየሩሳሌም እና በዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ  የምታካሂደው የሰፈራ ግንባታ ህገ ወጥ ነው ሲል ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ እሥራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ እየተወዛገቡ ነው ።  ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅ ን በድምጽ የመሻር መብትዋን ተጠቅማ ውሳኔው እንዳያልፍ አለማድረጓ እስራኤልን አስቆጥቷታል ። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ደግሞ ውሳኔውን እናስቀለብሳለን እያሉ ነው ። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው ብለዋል ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ