የአሜሪካ ም/ቤት የሰብዓዊ ጉዳዮችን የሚፈትሸዉን ረቂቅ አፀደቀ | ዓለም | DW | 11.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአሜሪካ ም/ቤት የሰብዓዊ ጉዳዮችን የሚፈትሸዉን ረቂቅ አፀደቀ

የአሜሪካ ኮንግረስ «ምክር ቤት» በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን የውሳኔ ሀሳብ ትላንት ለዛሬ አጥብያ አጸደቀ፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ ይጠይቃል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:50

ኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ ጥሪ አቅርቧል።

 

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ እና ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ የመብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይም ማዕቀብ እንዲጣል ይሻል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ እንዳይጸድቅ የኢትዮጵያ መንግስት ግፊት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ወኪላችን ልኮልናል። 
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ 
ሂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic