የአሜሪካ መንግሥት የገጠመው የበጀት ውዝግብ | ዓለም | DW | 22.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአሜሪካ መንግሥት የገጠመው የበጀት ውዝግብ

በዩኤስ አሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በሚወከሉት የሬፓብሊካውያን እና የዴሞክራቶች ፓርቲዎች እንደራሴዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት የሀገሪቱ መንግሥት እንቅስቃሴ ካለፉት ዓርብ  እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተቋርጧል። በፍልሰት እና ድንበር ፀጥታ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ሁለቱ ፓርቲዎች ያካሄዱት ክርክር የሚፈለገውን ወጤት አላስገኘም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:32

መፅደቅ ያልቻለው የበጀት ረ/ሕግ

እንደጎርጎሮሳዊው እስከ የፊታችን የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የመንግሥቱን ስራ እንዲያንቀሳቅስ ለምክር ቤቱ የቀረበው የበጀት ረቂቅ ሕግ በቂ የእንደራሴዎች ድምፅ ባለማግኘቱ ሳይፀድቅ ቀርቷል። ረቂቁ ሕግ እንዲያልፍ ከ100 የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች መካከል የ60ዎቹን ድምፅ ማግኘት አለበት። በመሆኑም በምክር ቤቱ 51 ወንበሮች ያሏቸው ሬፓብሊካውያን እንደራሴዎች ረቂቁ ሕግ ያልፍ ዘንድ በዴሞክራቶች ላይ ጥገኛ ናቸው። ረቂቁ ሕግ ያገኘው ግን የ50 እንደራሴዎችን ድጋፍ ብቻ ነበር።

የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት እንቅስቃሴ ሲቋረጥ ያሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ ባይሆንም፣ በሬፓብሊካውያን የሕግ መምሪያው እና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤቶች ፣ እንዲሁም፣ የዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት በተቆጣጠሩበት ጊዜ የተከሰተ የመጀመሪያው በመሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል።

የረቂቁ ሕግ አለማለፍ በመንግሥቱ እና በሕዝቡ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አሳርፏል? ረቂቁ ሕግ እንዳያልፍ እንደራሴዎቹን ያለያየው ምክንያት ምንድነው? እንደራሴዎቹ በረቂቁ ሕግ ላይ የተፈጠረውን ልዩነታቸውን ማጥበብ የሚችሉበት አግባቢ ሀሳብ ላይ ይደርሱ ይሆን? ለእነዚህ ጥያቄዎች የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ደበበ የሰጠውን ምላሽ  የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ናትናኤል ደበበ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ
 


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች