የአሜሪካዊዉ የኮፒዉተር አዋቂ ሞት | ዓለም | DW | 06.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካዊዉ የኮፒዉተር አዋቂ ሞት

ጠንካራ ሠራተኛ ነበሩ።አይበገሬ።ከርካሳ ጋራዥ ዉስጥ ጀምረዉ ሰዉ ከሚደርስበት ከሰዉም በጣም ጥቂት ሰዉ በዚሕ ዘመን ሊደርስበት የሚችልዉን የቴክኖሎጂ፥ የገንዘብ፥ የዝና ማዕረግ ጣራን ረመረሙት።ግን ያዉ ሰዉ ናቸዉ።እና ሞቱ።

default

ስቲቭ ጆብስ

06 10 11

በአሜሪካዊዉ የዘመናይ ኮሚዊተር አዋቂ ስቲቭ ጆብስ ዜና እረፍት የዓለም የኮፒዉተር ተጠቃሚዎችን በእጅጉ አሳዝኗል።ጆብስ ለኮፒዉተር ቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ በተለይ I Pad : I phon እና I Pod የተሰኙትን ትንሽ ፈጣን፥ ረቂቅና ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ የኮፒዉተር ሥልኮች መሳሪያዎችን የፈለሰፉ አዋቂ ነበሩ።አፕል የተሰኘዉ የኮምፒዉተር ኩባንያ ተባባሪ መስራችም ነበሩ።በነቀርሳ በሽታ ሞቱ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።

«ጠንክረን ሠራን።እና በአስር አመት ዉስጥ አፕል ጋራዥ ዉስጥ ከምንሰራ ሁለት ሰዎች ተነስቶ ባለሁለት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል እና የአራት ሺሕ ሠራተኞች ቀጣሪ ኩባንያ ሆኗል።»

ስቲቭ ጆብስ-1986 (እጎአ)።ከዚያ በሕዋላ በተቆጠረዉ ዘመን የጆብስ ምርምር፥ የኮሚዉተርን ቴክኖሎጂ እያረቀቀ፥ እያመጠቀ፥ የአፕልን ተወዳጅነት እያሻቀበ አዱኛን ቁል-አሰግዷል።በርጥግም ጠንካራ ሠራተኛ ነበሩ።አይበገሬ።ከርካሳ ጋራዥ ዉስጥ ጀምረዉ ሰዉ ከሚደርስበት ከሰዉም በጣም ጥቂት ሰዉ በዚሕ ዘመን ሊደርስበት የሚችልዉን የቴክኖሎጂ፥ የገንዘብ፥ የዝና ማዕረግ ጣራን ረመረሙት።ግን ያዉ ሰዉ ናቸዉ።እና ሞቱ።

«ዜና ዕረፍቱን ሥሰማ በጣም፥ በጣም ነዉ ያዘንኩት።ምክንያቱም እሱ ታላቅ ራዕይ የነበረዉ፥ የመገናኛዉን ዓለም የለወጠ ታላቅ ሰዉ ነበር።» አለች እሷ።አዉስትሬሊያዊዉ ስቴፋን ጃርጁራ በበኩሉ «የሱ ሞት ለኔ ልክ የማይክል ጃክሰንን፥ የልዕት ዳያናን ሞት የሰማሁ ዕለት ከደነገጥኩት እኩል ነዉ-ያስደነገጠኝ።» ይላል።

ሌላዉ ቀጠለ፥

NO FLASH Steve Jobs Apple Tod Todesfall

«ብርቅ ሰዉ ነበር።የአሜሪካ ብቻ አይደለም የመላዉ ዓለም ብርቅ ሰዉ እንጂ።እኔ እራሴ የሲልከን ቫሊ ሰዉ በመሆኔ በእሱ ግዙፍ ግዛት የተከበብኩ ነኝ።የሱ ዉርስ-ቅርስ።»

ከቶኪዮ-እስከ ሲንጋፑር ከቤጂንግ-እስከ ኒዉ ደልሒ፥ ከኒዮርክ እስከ ፓሪስ የኮሚዉተር መረብ ያስተሳሰረዉ ድፍን ዓለም በርግጥ አዘነ።የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ደግሞ ሁሉንም አሉት።«አብዛኛዉ የዓለም ሕዝብ የስቲቭን ሕልፈተ-ሕይወት የሰማዉ ራሱ ስቲቭ በፈጠረዉ መሳሪያ የመሆኑን ያክል የስቲቪን ስራ ዉጤት የሚመሰክር ነገር አይኖርም።» ብለዉ።

ዉልደት እድገታቸዉ ኋላ ከደረሱበት የመድረስ ጭላንጭል እንኳን የሚታይበት ዓይነት አልነበረም። ከግብፃዊ ሙስሊም ስደተኛ አባትና ከጀርመናዊት ስደተኛ እናት ሳንፍራንሲስኮ ዉስጥ ተወለዱ።እናት እና አባት አልተጋቡም።ሊጋቡ ሲፈልጉ የሴት ወገኖች እንቢኝ አሉ።እና ስቲቭ የአርመን ዝርያ ባላቸዉ ቤተሰቦች በጉዲፈቻ አደገ።

በመጀመሪያ እራሱን፥ ኋላ አካባቢዉን በስተመጨረሻዉ ዓለም የቀየረዉ ልጅ አንድ ትልቅ ሐብት ግን ድሮም ነበረዉ።ፅናት።

«በሆነ ነገር ማመን-መፅናት አለብሕ።በወኔሕ፥ በእጣ-ፈንታሕ፥ በሕይወት፥ ብቻ ባንድ ነገር።ምክንያቱም በነጠብጣቦች ማመን ነጥቦቹ ሲገጣጠሙ ከትልቁ ጎዳና ይዶላሉ።ባረጀ አቅጣጪያ ቢያጉዝሕ እንኳን ፅናት ካለሕ ልብሕ ያሰበዉን እንድትከተል በራስ የመተማመን መንፈስ ያጎናፅፍሐል።»

Steve Jobs Flash-Galerie

በርግጥም ሰዉዬዉን መሬት ላይ ከመተኛት-ወደ ተንደላቀቀ ኑሮ፥ ከኮሌጅ ጥሎ ከመዉጣት ወደ ትልቅ አዋቂነት፥ የኮካላ ጠርሙስ ከመሽጥ ወደ ዓለም ግዙፍ ኩባንያ ባለቤትነት ያደረሰዉ ፅናት እምነቱ ነዉ።ነቀርሳ ግን በቃ-አሸነፋቸዉ።የአራት ልጆች አባት ነበሩ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌAudios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች