የአሜሪካዉዊዉ ጋዜጠኛ መገደልና ተቃዉሞ | ዓለም | DW | 03.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአሜሪካዉዊዉ ጋዜጠኛ መገደልና ተቃዉሞ

ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ጄምስ ፎሌይ የተባለ ሌላ አሜሪካዊ ጋዜጠኛን በተመሳሳይ መንግድ ገድሎ ነበር። ግድያዉ ያስቆጣቸዉ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ መንግሥት በቡድኑ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስድ እየጎተጎቱ ነዉ።

የኢራቁ አሸባሪ ቡድን (ISIS) ከዚሕ ቀደም አግቶት የነበረዉን አሜሪካዊ ጋዜጠኛ መቅላቱ የዩናትድ ስቴትስ ፖለቲከኞችን፤መገናኛ ዘዴዎችንና ተራዉን ሕዝብ ጭምር አስቆጥቷል። ISIS ጋዜጠኛ ስቴቫን ሶትሎፍን የገደለዉ ዩናይትድ ስቴትስ የአማፂዉን ቡድን ይዞታ በጦር ጄቶች መደብደቧን እንድታቆም በተደጋጋሚ የሠጠዉን ማስጠንቀቂያ «አልተቀበለችም» በሚል ሰበብ ነዉ። ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ጄምስ ፎሌይ የተባለ ሌላ አሜሪካዊ ጋዜጠኛን በተመሳሳይ መንግድ ገድሎ ነበር። ግድያዉ ያስቆጣቸዉ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ መንግሥት በቡድኑ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስድ እየጎተጎቱ ነዉ። የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀን ሥለ ጉዳዩ በሥልክ አንጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

 

Audios and videos on the topic