የአሜሪካን ወታደሮች የአፍጋኒስታን ቆይታ መራዘም | ዓለም | DW | 16.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካን ወታደሮች የአፍጋኒስታን ቆይታ መራዘም

ኦባማ እንዳሉት የወታደሮቹ ቆይታ የተራዘመው የአፍጋኒስታንን መንግሥት የሚወጋው ፅንፈኛው ታሊባን በሃገሪቱ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን እያደረሰ በመሆኑ ምክንያት ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:16

የአሜሪካን ወታደሮች የአፍጋኒስታን ቆይታ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አፍጋኒስታን የዘመተው የአሜሪካን ሠራዊት ቆይታ መራዘሙን ትናንት አስታወቁ ። ከዚህ ቀደም እንደታሰበው የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት የአሜሪካን ሠራዊት ከአፍጋኒስታን ጠቅልሎ ወደ ሃገሩ እንደማይመለስ ኦባማ ተናግረዋል ።ኦባማ እንዳሉት የወታደሮቹ ቆይታ የተራዘመው የአፍጋኒስታንን መንግሥት የሚወጋው ፅንፈኛው ታሊባን በሃገሪቱ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን እያደረሰ በመሆኑ ምክንያት ነው ።በአሁኑ ጊዜ በአፍጋኒስታን ከ9 ሺህ በላይ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ይገኛሉ ።የዚህ ሠራዊት ቁጥር በጎርጎሮሳዊው 2017 መጀመሪያ ላይ ወደ 5500 ዝቅ ይደረጋል ተብሏል ።የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በኦባማ ውሳኔ ተደስቷል ።የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር አገባ ልኮልናል ።
ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic