የአሜሪካን ም/ቤት ዉሳኔን ኢትዮጵያ ተቃወመች | ኢትዮጵያ | DW | 11.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአሜሪካን ም/ቤት ዉሳኔን ኢትዮጵያ ተቃወመች

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት (ኮንግረስ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚጠይቀዉን ረቂቅ ዉሳኔ ትናንት ማፅደቁን ኢትዮጵያ አጥብቃ ተቃወመች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:30

ዉሳኔዉ“የአሜሪካ እና የኢትዮጵያን የጋራ ጥቅም ከግምት ውስጥ ያላስገባ ”ነዉ

የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ የታሰሩ እንዲፈቱ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ የሚጠይቀውን «ኤች አር 128 » የተባለውን ረቂቅ ውሳኔ ማጽደቁን የኢትዮጵያ መንግሥት አጣጣለ። ዶቼ ቬለ ያነጋጋገራቸዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም  በመንግስትም ሆነ በገዥዉ ፓርቲ በኩል የተለያዩ ጉዳዮች እየተሰሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኤች አር 128 መጽደቁ “ወቅቱን ያልጠበቀና ያልተገባ ነው” ብለዋል። የኤች አር 128 የውሳኔ ሀሳብ ከመግለጫነት ባለፈ ሕጋዊ ትርጉምና አንዳችም ተፅእኖ እንደሌለው ተናግረዋል። አቶ መለስ ዓለም፤ መንግሥት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ምንም እንከን የለም የሚል አቋም የለዉም ሲሉም ተናግረዋል።  

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic