የአሜሪካና የቻይና ፉክክር በአፍሪቃ | ዓለም | DW | 09.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካና የቻይና ፉክክር በአፍሪቃ

የዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂልሪ ክሊንተን፤ በ 11 ቀናት ውስጥ 7 የአፍሪቃ አገሮችን ጎብኝተዋል። ወደ ናይጀሪያ ብቅ ያሉት ክሊንተን የአፍሪቃውን ዙር ጉብኝታቸውን የሚደመደሙት ነገ ነው። ክሊንተን በጉዞአቸው፤ የአፍሪቃን መንግሥታት፣ «ማልማት ሳይሆን መቦጥቦጥ ከሚወዱ ተባባሪ መንግሥታት ተጠንቀቁ »

የዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂልሪ ክሊንተን፤ በ 11 ቀናት ውስጥ 7 የአፍሪቃ አገሮችን ጎብኝተዋል። ወደ ናይጀሪያ ብቅ ያሉት ክሊንተን የአፍሪቃውን ዙር ጉብኝታቸውን የሚደመደሙት ነገ ነው። ክሊንተን በጉዞአቸው፤ የአፍሪቃን መንግሥታት፣ «ማልማት ሳይሆን መቦጥቦጥ ከሚወዱ ተባባሪ መንግሥታት ተጠንቀቁ » ማለታቸው ተጠቅሷል። መልእክቱ እንደሚመለከታት የተሰማት ቻይና፣ በበኩሏ ዩናይትድ እስቴትስን መንቀፏ አልቀረም። ያም ሆነ ይህ ሁለቱ መንግሥታት፣ በአፍሪቃ ላይ ያላቸው ስልታዊ አቋም፣ ለዶቸ ቨለ ቀጣዩን ዘገባ ያቀረበው ፊሊፕ ሳንድነር እንዳለው አይለያይም። ሳንድነር የላከውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
ከዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተሰነዘረው ቃል ከረር ያለ ነው። ክሊንተን የአፍሪቃውን ጉብኝታቸውን በሴኔጋል መዲና በዳካር ሲጀምሩ ባሰሙት ቃል፤አገራቸው በአፍሪቃ ዴሞክራሲ እንዲገነባና ሰብአዊ መብት እንዲከበር የምትሻ መሆኗን ነው የተናገሩት። በማያያዝ፤ እያንዳንዱ ተባባሪ ሀገር ለአፍሪቃ እንዲህ አያስብም ነው ያሉት። የቻይና ዜና አገልግሎት ቺንሁዋ፣ ክሊንተን ፤ በቻይናና አፍሪቃ መካከል ያለውን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ የግንኙነት ገመድ ለመበጠስ ነው የፈለጉት

ብሏል። ግን ፣ ሁለቱ መንግሥታት በአፍሪቃ ላይ ያላቸው አቋም እስከምን ድረስ ነው የሚለያየው? የኦባማ አስተዳደር በአፍሪቃ ቅድሚያ የሚሰጠው ከኤኮኖሚ ትብብር ይልቅ ለዴሞክራሲ መሆኑን ነው የሚናገረው። በፕሪቶሪያ ፣ ደቡብ አፍሪቃ፤ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ተቋም ባልደረባ ጃኪ ሲልዬ እንደሚሉት ደግሞ ፣ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ትብብር ፣ አሁንም ወሳኝ ሚና አለው፣።
«ማሊን በመሳሰሉ አገሮች፤፣እንዲሁም በሌላው የአኅጉሩ ከፊል፣ ሱዳንና ሶማሌን በመሳሰሉ አገሮች ለመረጋጋት ዋስትና ማስገኘት ወሳኝነት አለው። በሰሜን አፍሪቃ እንደሚታየው፤መንግሥታዊ ተቋማትን ማደራጀቱ ነው ዘላቂ መረጋጋትን ሊያስከትል የሚችለው»።
ቻይና ፣ በሌሎች አገሮች የመልካም አስተዳድር ይዞታና ሰብአዊ መብት አያስጨንቃትም ይባላል። BRICS በሚል የአንግሊዝኛ ምኅጻር የታወቀው ብራዚል፤ ሩሲያ ህንድና ደቡብ አፍሪቃ የተሠሠሩበት ድርጅት፣ የልማት እርዳታን ፤ ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ፤ የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችን ቅድመ ግዴታ ፤ እንደሚባለው ፤ ሆን ብለው ይቃወሙታል። ቻይና በሌላው አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አልገባም እንደምትልም ነው የሚነገረው። የዩናይትድ እስቴትስ አስተዳደር፣ በቅርቡ በምሥራቅ የኮንጎ ሪፓብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ትደግፋለች በማለት ለሩዋንዳ የሚሰጠው የአርዳታ ገንዘብ እንዲቀነስ አድርጓል። በ Würzburg ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ፣ ፊሊፕ ጊግ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ ለመላካም አስተዳደር የቆምኩ ነኝ ማለቷን ይነቅፋሉ። እንደርሳቸው አባባል አሜሪካ ይህን የምታደርገው

ማድረግ በምትፈልገው አካባቢ ብቻ ነው። አንድ ምሳሌ ፤ ኢትዮጵያ ናት። በአፍሪቃው ቀንድ የምትገኘው ሀገር፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በሶማልያ ለሚደረገው ፀረ አሻባሪነት ትግል ፤ አጋር ናት ይላሉ፣ ጊግ።
«ስለሆነም፤ ዩናይትድ እስቴትስ፣ በኢትዮጵያ ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ መሰንዘሩን አትቃጣውም። አታደርገውም። ከጥቅም አኳያ ምክንያቱን መገንዘብ ይቻላል። በሌላ በኩል ግን፤ የክሊንተንን ሃሳብ በሌላ መልኩ ነው ማየት የሚቻለው ። አሜሪካውያን ለዴሞካራሲና መልካም አስተዳደር ነው የቆምን ሲሉ ፤ በአርግጥ ኢትዮጵያን ማለታቸው እንዳልሆነ በግልጽ ነው የሚታየው።»
የ ፀጥታ ጥናት ተቋም (ISS) ባልደረባ ፣ ጃኪ ሲልዬ የቀድሞዋ ኃያል መንግሥትና የአሁኗ ፣ ዩናይትድ እስቴትስና ቻይና፤ በአንድ ነጥብ ይስማማሉ። አፍሪቃ ያለውን ሰፊ የማደግ ዕድል በመገንዘብ፣ በዚሁ የኤኮኖሚ እንቅሥቃሴ ራሳቸው ለማትረፍ ነው ታጥቀው የተነሱት።
«ዩናይትድ እስቴትስና ቻይና በአፍሪቃ ገበያ የሚያደርጉት ውድድር እየጠረከረ ነው የመጣው። አፍሪቃ ፣ጠቃሚ የንግድ ተባባሪ እንጂ፤ አሜሪካዊ ሰብእና እንዲላበስ ብቻ አይደለም ከአሜሪካ የሚፈለገው።»
የደቡብ ነፋስ የተሰኘው ተቋም፣ በአውሮፓው ኅብረት ጥያቄ ባካሄደው ምርምር መሠረት 46 ከመቶው የቻይና የልማት እርዳታ የሚፈሰው ለአፍሪቃ ነው። የሚሰጥ ብድር ለየትኛው ፕሮጀክት እንደሚውል የጋራ ስምምነት ተደርጎበት ነው። መሠረታዊ ልማት ላይ ለምሳሌ ያህል ቻይናውያን ኩባንያዎች ተሳታፊዎች ነው የሚሆኑት።

አንዳንዴም ተባዳሪዎቹ አገሮች ብድሩን መልሰው የሚከፍሉት ጥሬ ሀብት በማቅረብ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞም ፤ የአፍሪቃ አገሮች ርካሽ ረጋ ሠራሽ የቻይና ሸቀጣ ሸቀጥ ማራጋፊያ ገበያ እየሆኑ ይገኛሉ።«ይህ የተዛባ ፤ ያልተስተካከለ የንግድ ልውውጥ፣ የተለመደው የንግድ ዓይነት ነው። ይህም ቀደም ባለው ዘመን፤ በቅኝ ተገዥዎችና በቅኝ ገዥዎች የነበረ ዓይነት ግንኙነት ነው። ይህ እንግዲህ በአፍሪቃና በቻይና ብቻ የተከሠተ ንግድ አይደለም። በአሜሪካና በአፍሪቃ ንግድ ልውውጥም፣ ወይም በአውሮፓና በአፍሪቃ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥም ያው አንድ ዓይነት ነው።»
ባለሀብቶች ወይም ባለወረቶች ገንዘባቸውን አፍሪቃ ውስጥ ሥራ ላይ ማዋላቸው በረጅም ጊዜ አቅድ ፤ አፍሪቃውያን ሊያስቡበት ይገባል በማለት ፊሊፕ ጋይግ ያስጠነቅቃሉ። ባጋደለ መልኩ ቻይናን ብቻ ማውገዙ ትክክል አይሆንም። የደቡብ -ደቡብ ትብብር፣ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ነው የሚነገርለት።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 09.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15nGz
 • ቀን 09.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15nGz