የአሜሪካና የተባባሪዎችዋ ድብደባ | ዓለም | DW | 24.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአሜሪካና የተባባሪዎችዋ ድብደባ

የሶሪያ ጉዳይ ታዛቢ የተሰኘዉ ቡድን እንደዘገበዉ ትናንት በተጀመረዉ ድብደባ 120 የሁለቱ ቡድናት አባላት እና 8 ሠላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።

የዩናትድ ስቴትስና የተባባሪዎችዋ ሐገራት የጦር አዉሮፕላኖች ዛሬም እንደትናቱ የአሸባሪ ቡድናት ይዞታ የተባሉ የሶሪያ ግዛቶችን ሲደበድቡ አነጉ።የሶሪያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎችና የሶሪያ ጉዳይ ታዛቢ የተሰኘዉ ቡድን በየፊናቸዉ እንዳሉት የአሜሪካ መራሹ ጦር ተዋጊ ጄቶች በተለይ ሶሪያን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስነዉን ድንበር እና አሌፖ የተባለችዉ ከተማ አካባቢን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።ዘገባዎቹ እንደጠቆሙት ሶሪያን ከኢራቅ ጋር በሚያዋስነዉ አልቡ ከማል በተባለችዉ ከተማ አካባቢዊ የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ፅንፈኛ ቡድን፤ አሌፖ አጠገብ የምገኝዉ አይን አ አረብ ደግሞ አል-ኑስራ የተሠኘዉ ሌለኛዉ ፅንፈኛ ቡድን የመሸጉበት ነዉ።የሶሪያ ጉዳይ ታዛቢ የተሰኘዉ ቡድን እንደዘገበዉ ትናንት በተጀመረዉ ድብደባ 120 የሁለቱ ቡድናት አባላት እና 8 ሠላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ