የአሜሪካና የሩሢያ የጦር መሣሪያ ቅነሣ ውል | ዓለም | DW | 08.04.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካና የሩሢያ የጦር መሣሪያ ቅነሣ ውል

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማና የሩሢያው የሥልጣን አቻቸው ዲሚትሪይ ሜድ’ቬዴቭ ከሁለት አሠርተ-ዓመታት ወዲህ ታላቅ የሆነ የኑክሌያር ጦር መሣሪያ ቅነሣ ውል ዛሬ ፕራግ ውስጥ ተፈራረሙ።

default

ዘመኑ ያከተመውን የ 1991 ዓ.ም. ስታርት-ስምምነት የሚተካው አዲስ ውል የሁለቱን ሃያል መንግሥታት የኑክሌያር አረሮች መጠን በ 1,550 ጣራ የሚገድብ ነው። እርግጥ ሩሢያ አሜሪካ በማዕከላዊው አውሮፓ የሮኬት መከላከያ ዘዴ ለመትከል ያላት ዕቅድ አስጊ ሆኖ ከታያት አዲሱን ውል የማፍረስ መብቷን አስጠብቃ ነው ስምምነቱን የምትፈርመው። ለፊርማው ፕራግ መመረጧ ደግሞ ኦባማ ከአንድ ዓመት በፊት ከአቶም መሣሪያ ነጻ የሆነች ዓለም ራዕያቸውን ያብራሩባት ስፍራ በመሆኗ ነው። ከበርሊን፤

ይልማ/ሃይለ ሚካዔል!

መስፍን መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic