የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ሽኝት እና የቀብር ስነ ስርዓት | ኢትዮጵያ | DW | 26.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ሽኝት እና የቀብር ስነ ስርዓት

በዚሁ የሽኝት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች እና የውጭ ሃገራት ተጠሪዎች የሟቾቹ ቤተሰቦች እና የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የክልሉ የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ደግሞ ዛሬ ላሊበላ ተቀብረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58

የአማራ ክልል አመራሮች ሽኝት እና የቀብር ስነ ስርዓት

 
 የመንግሥት ግልበጣ በተባለ ጥቃት የተገደሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪያቸው የአቶ አዘዘው ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የአቶ ምግባሩ ከበደ ሽኝት እና የቀብር ስነስርዓት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ተኪሂዷል። በባሕር ዳር ስታድዮም በተካሄደው በዚሁ የሽኝት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የውጭ ሃገራት ተጠሪዎች የሟቾቹ ቤተሰቦች እና የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በሌላ በኩል በክልሉ ተካሄደ የተባለውን መፈንቅለ መንግሥት አቀናብረዋል የተባሉት የክልሉ የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ደግሞ ዛሬ ላሊበላ ተቀብረዋል። ዓለምነው መኮንን ከባህር ዳር ዘገባ ልኮልናል።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic