የአማራ ክልል መምሕራን ጥያቄ | ኢትዮጵያ | DW | 31.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአማራ ክልል መምሕራን ጥያቄ

የክልሉ መምሕራን ማሕበር በጠራዉ ሠልፍ የክልሉን ርዕሠ ከተማ የባሕርዳርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች መምሕራን በየአካባቢያቸዉ ተሰልፈዉ አርፍደዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:06

የአማራ መምሕራን ጥያቄ

የአማራ መስተዳድር መምሕራን ጥቅምና መብታቸዉ እንዲከበር፣ የትምሕርት ጥራት እንዲሻሻልና በተለያዩ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንዲቆሙ ዛሬ ባደባባይ ሠልፍ ጠየቁ።የክልሉ መምሕራን ማሕበር በጠራዉ ሠልፍ የክልሉን ርዕሠ ከተማ የባሕርዳርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች መምሕራን በየአካባቢያቸዉ ተሰልፈዉ አርፍደዋል።የማሕበሩ መሪዎች እንዳስታወቁት በሰልፉ የመምሕራን ኮሎጆች፣የቴክንኒክና የሙያ ትምሕርት ቤቶች፣ በየደረጃዉ የሚገኙ የአጠቃላይ ትምሕር ቤቶች መምሕራን በየሰልፉ ተካፍለዋል።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን እንደዘገበዉ ባሕርዳር አደባባይ የወጡት መምሕራን በሺሕ ይቆጠራሉ።የአማራ ርዕሠ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ የመምሕራኑን ጥያቄ በየደረጃዉ ላሉ የመንግስት ሹማምንታት ለማቅረብ ቃል ገብተዋል።

አለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic