የአመት እረፍት ባህል በጀርመን | ባህል | DW | 01.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የአመት እረፍት ባህል በጀርመን

ጠንክሮ መስራትን ባህሉ ያደረገዉ የጀርመን ህዝብ፣ በአመት ዉስጥ እረፍት የመዉሰድ ባህልንም ግዴታ በማድረግ ባህሉ አድርጎታል። በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ አሁን ባለዉ የበጋዉ ወራት ለእረፍት ቤተሰቦቻቸዉን ይዘዉ ከአገር ከመኖርያ ቤታቸዉ ወጣ ያሉ ሁሉ የእረፍት ግዜያቸዉን በማጠናቀቅ ወደ የስራ እና ወደ ትምህርት ቤቶቻቸዉ እየተመለሱም ነዉ።

default

በተለያዩ አለም ክፍሎች የሚገኙ አገሮች የአመት እረፍት አወሳሰድ ደንቡ ቢለያይም በተለይ በምዕራባዉያኑ ዘንድ አንድ ሰራተኛ የአመት እረፍት የመዉሰድ ግዴታ ስላለበት፣ ለእረፍት የሚሰጡት ትርጉም ለየት ያለ መሆኑን ያሳያል። በሌላ በኩል በጀርመን ከልጅነት ጀምሮ የማንበብ ባህልን የሚካነዉ ህጻን በተጓዳኝ፣ መረጃ የመስጠት የመቀበል ባህልን ይማራል፣ በመቀጠል የስራ ባህልን በስራ ፍሪያማ ለመሆን እረፍትንም ይማራል። በእረፍቱ ሰአት የሰራዉን ያየዉን ነገር በመጸሃፍ መልክ፣ በፎቶግራፍ መልክ መረጃን በማስቀመጥ አዲስ ባህልን አዲስ ቦታን አይቶ ለሌላዉም ያስተላልፋል። በጀርመን አገር ያሉ መምህራንም ተማሪዎቻቸዉ ከእረፍት ሲመለሱ፣ በእረፍት ግዜያቸዉ አዲስ ነገር ያዪትን እንዲተርኩ ያደርጋሉ። በለቱ ዝግጅታችን በጀርመን በበርሊን አካባቢ የዘረኝነት ጥላቻን እና የቀኝ አክራሪዎችን ጥላቻ ለመግታት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ አመት የክብር ሜዳልያ ከጀርመንዋ መራሂተ መንግስት ቢሮ የተቀበሉት እና ከሁለት አስርተ አመታት በላይ በበርሊን ነዋሪ የሆኑትን ዶክተር መኮንን ሽፈራዉን እና በበርሊን ከተማ በሚገኘዉ ሁንቦልት ዪንቨርስቲ በማህበረሰብ ጥናት ሞያ ምሩቅ እና በሃይማኖት ትምህርት ተቋም ዉስጥ ድረ-ገጽ ባለሞያ የሆኑትን ጀርመናዊዉን ሚሻኤል ኦቶን በጀርመን ስለሚታየዉ የአመት እረፍት ባህል ጠይቀናቸዋል፣ ሙሉዉን መሰናዶ ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic