የ«አልፋ-ቤት ኢትዮጵያ» ማሕበር በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የ«አልፋ-ቤት ኢትዮጵያ» ማሕበር በጀርመን

መቀመጫውን ጀርመን ያደረገው የ«አልፋ-ቤትኢትዮጵያ»ማሕበርበተለይ በኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን ያንበሊ አካባቢ ታዳሽ የሀይል ምንጭ ለአካባቢው ነዋሪዎች በማቅረብ ይንቀሳቀሳል። ይኼው ማህበር ከሁለት ሳምንታት በፊት ባዘጋጀው ስብሰባ የንጹህ ውሀ አቅርቦት እና የዕውቀት ሽግግር ቀጣዩ አላማው እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህ በጀርመን የተለያየ አላማ ነድፈው የተመሰረቱ የኢትዮጵያውያን ወይም ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ያላቸው ማህበሮች ተቋቁመዋል። የባህል፣ የስፖርት፣ የተማሪዎች ፣ የበጎ አድራጎት እና ሌሎችም። አቶ ሳሙኤል ኤታና የ«አልፋ-ቤትኢትዮጵያ»ማህበር ሊቀመ መንበር ናቸው። በደቡብ ምዕራብ ጀርመን የሚገኘው ማህበር የተመሰረተው እኢአ በ 2008 ዓም ነው።

ታዳሽ የኃይል ምንጭ በተለይም ከፀሐይ የሚገኘው ኃይል ኢትዮጵያ ውስጥም በአገልግሎት ላይ ሲውል ተስተውሏል። ይህንን ቴክኖሎጂ እና እውቀት ወደ ሀገሪቱ በማስገባት ምቹውን የአየር ንብረት ይበልጥ መጠቀም ይቻላል። የኤሌክትሪክ ሥራ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል፤ የ«አልፋ-ቤትኢትዮጵያ»ማህበር ከተመሰረተ አንስቶ በዚሁ ረገድ በተጨባጭ ስለፈፀማቸው ስራዎች ገልጸውልናል።

የ«አልፋ-ቤት ኢትዮጵያ ማሕበር በዚህ በጀርመን ሀገር ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ላይ ማህበሩ እቅዱን አስተዋውቋል። በውጭ ሀገር የቀሰሙትን እውቀት ከቴክኖሎጂው አፈጻጸም ጋር ለያንበሊ ነዋሪዎች ጎን ለጎን ለማካፈል ማህበሩ አምኖበት ተነስቷል።ይህም የሰዎች እውቀት በጨመረ ቁጥር ፍላጎታቸውም የዛኑ ያህል ስለሚጨምር ነው።

የ«አልፋ-ቤት ኢትዮጵያ »ማህበር አባላት ከ 20-25 ይሆናሉ የሚሉት አቶ ሳሙኤል ለያንበሊ ነዋሪዎች ስልጠና እስኪጀምሩ ድረስ እስካሁን ለተገጠሙት በፀሀይ የሚሰሩ ታዳሽ ኃይል መሣሪያዎች ማን ክትትል እንደሚያደርግም ገልፀውልናል።

ሙሉውን ዝግጅት በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic